በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊባኖስ የባንክ ደንበኞች በኃይል ገንዘባቸውን በማውጣት ላይ ናቸው


ሊባኖስ
ሊባኖስ

ባንኮቿ የገንዘብ እጥረት ባጋጠማቸው ሊባኖስ ያሉ የባንክ ደንበኞች በሃገሪቱ በሚገኙ ባንኮች በጉልበት እየገቡ ገንዘባቸውን በመጠየቅና በማስወጣት ላይ ናቸው።

በሊባኖስ ባንኮች ለአንድ ሳምንት ዝግ ሆነው ቆይተው የነበረ ሲሆን፣ አሁን በከፊል ክፍት ናቸው።

የኢኮኖሚ ቀውስ ሀገሪቱን እያሽመደመደ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በርካታ ደንበኞች ወደ ባንክ በኃይል በመግባት ገንዘባቸውን በማውጣት ላይ ይገኛሉ። ባንኮቹ ደንበኞቻቸው የተወሰነ ገንዘብ ብቻ እንዲያወጡ ነው የሚፈቅዱት።

ድርጊቱ ዜጎች በሙስና በተበላሸውና ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት ኢኮኖሚ ምክንያት በባለሥልጣናት እና በባንኮቹ ላይ ያላቸውን ብስጭት ያሳያል ተብሏል።

“ከመቶ ዓመት ወዲህ ያልታየ” ብሎ የዓለም ባንክ በሚገልጸው ደረጃ፣ ሦስት እጅ የሚሆኑ ሊባኖሳውያን በድህነት አረንቋ ውስጥ ይገኛሉ። የሊባኖስ ፓውንድ 90 በመቶ የሚሆነውን ዋጋውን በማጣቱ፣ ሚሊዮኖች ሰማይ የደረሰው የሸቀጥ ዋጋ የማይቀመስ ሆኖባቸዋል።

አሊ አል-ሳሂሊ የተባለ የቀድሞ ፖሊስ አባል፣ ቢኤልሲ ወደተባለው ባንኩ በመሄድ ተቀማጭ የነበረውን 24 ሺህ ዶላር የትምህርት ቤት ክፍያና የቤት ክራይ ዕዳ ላለበትና በዩክሬን ለሚገኘው ልጁ እንዲላክ በማስፈራራት ጠይቋል።

“አንዳችሁ ከመሞታችሁ በፊት ገንዘቡን ቁጠሩ” ብሏል አሊ አል-ሳሂሊ፣ የቀድሞው ፖሊስ አባል ለባንክ ሠራተኞች፤ በአንድ እጁ በስልክ እየቀረፀ፣ በሌላ እጁ ሽጉጡን እያወዛወዘ።

“የገንዘብ አስቀማጮች ጩኽት” ብለው የሚጠሩት የተቃውሞ ቡድን እንዳለው፣ ባንክ ገንዘቡን ለማዘዋወር ለወራት ባለመፍቀዱ፣ አሊ አል-ሳሂሊ በዩክሬን የሚገኘው ልጁን ለመደገፍ ኩላሊቱን ለመሸጥ ተዘጋጅቶ ነበር።

አሊ አል-ሳሂሊ በቀረጸው ቪዲዮ እንደታየው፣ ሽጉጡን እያወዛወዘ፣ ትዕዛዙን የማይቀበሉ ከሆነ እንድሚተኩስ የባንክ ሠራተኞችን አስፈራርቷል። አሊ አል-ሳሂሊ የጠየቀውን ገንዘብ አላገኘም። ሠራተኞቹ እያረጋጉት ከቆየ በኋላ፣ የፀጥታ ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር አውለውታል።

ታይር በተባለችው የደቡብ ከተማ ግን አንድ ደንበኛ 40 ሺህ ዶላር ለማውጣት በሽጉጥ አስፈራርቶ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ከተኮሰ በኋላ፣ የፀጥታ ሠራተኞች ቢመጡም ፍጥጫው ቀጥሎ፤ በኋላ በተደረገ ድርድር 9 ሺህ ዶላር ማውጣት ችሏል።

በሌሎች የሃገሪቱ ክፍልም፣ አንዳንዶቹ ሙከራዎች ሲሳኩ፣ ሌሎቹ ደግሞ በፀጥታ አስከባሪዎች መድረስ ከሽፈዋል።

አንዳንድ የባንክ ደንበኞችና፣ “የገንዘብ አስቀማጮች ጩኽት” ብለው የሚጠሩት የተቃውሞ ቡድን በጉልበት ገንዘብ የማስወጣቱን ድርጊት በማበረታታት፣ ወደፊትም እንደሚቀጥል ዝተዋል፡

XS
SM
MD
LG