በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በደራሼ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በተከሰተ ግጭት ቁጥራቸው የበዛ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ ሲቪሎች መገደላቸው እና መፈናቀላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። ከጂንካ ወደ አርባ ምንጭ ሲጓዙ የታገቱ የውጭ አገር ዜጎች መለቀቃቸውና እነሱን ለማስለቀቅ የተንቀሳቀሱ የደቡብ ክልል ፀጥታ ኃሎችም ከአጋቾች በተሰነዘረባቸው ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ በአከባቢው በተደጋጋሚ የሚነሳው ግጭት የብዙ ዜጎች ህይወት እየተቀጠፈ መሆኑን ገልጾ መንግሥት የሃገርና የሕዝቡን ደህንነት ማስጠበቅ ተቀዳሚ እና ዋና ተግባሩ አድርጎ እንዲሠራ ጥሪ አቅርቧል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።