በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የተመድ ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን አስከሬን ወደ ጋና ተወሰደ

በቅርቡ ያረፉት የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን አስከሬን በመንግሥታዊ የቀብር ሥነ ስርዓት ወደሚያርፍበት ወደትውልድ ሃገራቸው ወደ ጋና ተወስዷል።

በቅርቡ ያረፉት የቀድሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ኮፊ አናን አስከሬን በመንግሥታዊ የቀብር ሥነ ስርዓት ወደሚያርፍበት ወደትውልድ ሃገራቸው ወደ ጋና ተወስዷል።

የጋና ፕሬዚደንት ናና አዶ ዳንክዋ አኩፎ አዶ የሙዋቹን ባለቤት ኔኔ አናንና ቤተሰባቸውን አክራ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የፊታችን ሃሙስ የሚከናወን ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ህዝቡ በአክራ ዓለምቀፍ የጉባዔ ማዕከል እየተገኘ አክብሮቱን ይገልፃል።

የኖቤል ተሸላሚው የመጀመሪያው አፍሪካዊ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሓፊ በተወለዱ በሰማኒያ ዓመታቸው ስዊዘርላንድ በርን ከተማ ውስጥ ነው ያረፉት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG