በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄይቲን የተደራጁ የወሮበላ ቡድኖች ሁከት ለማስቆም የሚረዱ የኬኒያ ፖሊሶች ፖርት ኦ ፕሪንስ ገቡ


በሄይቲ በሚፈጠረው ግጭት ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለዋል ተሰደዋል፤ በፖርት-አው-ፕሪንስ፣ ሃይቲ እአአ ነሀሴ 15/2023
በሄይቲ በሚፈጠረው ግጭት ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለዋል ተሰደዋል፤ በፖርት-አው-ፕሪንስ፣ ሃይቲ እአአ ነሀሴ 15/2023

አስራ ሁለት የኬኒያ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ትናንት ዕሁድ ሄይቲ ዋና ከተማ ፖርት ኦ ፕሪንስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ እንደደረሱ በብረት ለበስ ተሽከካሪዎች ታጅበው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ተወስደዋል፡፡

ኬኒያ ‘የወሮበላ ቡድኖችን ሁከት ለመግታት የሄይቲን ብሔራዊ ፖሊስ እረዳለሁ’ ማለቷን ተከትሎ የተጓዙት ኬኒያውያኑ የፖሊስ መኮንኖች አስቀድመው የቅኝትና ምርመራ ተልዕኮ እንደሚያከናውኑ ዘገባው አመልክቷል፡፡

ባለፈው አርብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ባለስልጣናት “እጅግ የበረታ ጭካኔ የተመላበት” ያሉትን ሄይቲ ውስጥ በተደራጁ የወሮበላ ቡድኖች የሚፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።ሁከቱ እየተባባሰ በመምጣቱ በሺዎች የተቆጠሩ የመዲናዋ ፖርት ኦ ፕሪንስ ነዋሪዎች ከተማይቱን እየለቀቁ በመውጣት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዐዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ራቪና ሻምዳሳኒ እንደተናገሩት ሄይቲ ውስጥ ከዚህ እአአ ከ2023 መጀመሪያ እስከ ነሃሴ 15 በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ2400 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል፡፡ ከ950 በላይ ተጠልፈዋል፡፡ ሌሎች 902 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ኬኒያ የሰው እና የገንዘብ እና ሌላም አቅም ዕጥረት ያለበትን የሄይቲ ፖሊስ ሰራዊት ለመርዳት የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጥረት የመምራቱን ሓላፊነት ለመውሰድ ፈቃደኝነቷን መግለጿ ይታወሳል፡፡ ከ11 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሄይቲ ያሏት ፖሊሶች 10 ሺህ ገደማ ብቻ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG