በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ 35 ኩባንያዎችን ወደ ግል ልታዞር ነው


ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ

የኬንያ መንግሥት በይዞታው ሥር ያሉ 35 ኩባንያዎችን ለግል መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለፈው ወር የመንግሥት ቢሮክራሲን ለመቀነስ በሚል ያወጡትን ህግ አስመልክተው ትናንት (ሐሙስ) ሲናገሩ በዝርዝር ባይጠሯቸውም የተጨማሪ መቶ ኩባንያዎች ጉዳይም እንደሚታይ አስታውቀዋል።

አዲሱ ህግ የመንግሥት ኩባንያዎችን ወደ ግል የማዛወሩ ሂደት ማንም ሰው ከድርጅቶቹ ድርሻ ወይም አክስዮን መግዛት እንዲችል ለህዝብ ክፍት በማድረግ ወይም ግልፅ ጨረታ በማውጣት እንዲሸጡ ያዝዛል።

ኬንያ ከአሁኑ እርምጃዋ ቀደም ሲል በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩ ተቋማትን ወደ ግል ያዛወረችው የዛሬ 15 ዓመት ሲሆን ያኔ የሳፋሪኮምን የቴሌኮሙኒኬሽን ሽያጭ 25 ከመቶ ለህዝብ ግዥ ክፍት በማድረግ ወደግል ይዞታነት ቀይራለች።

የዛሬ 14 ዓመት ደግሞ የነዳጅ ማስተላለፊያ ኩባንያን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ኩባንያንና ባንኮችን ጨምሮ የ26 ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት እንዲዞሩ የሀገሪቱ ካቢኔ ቢወስንም እስካሁን የተከናወነ እርምጃ እንደሌለ ታውቋል።

ኬንያ ለከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ፈተናዎች እየተጋፈጠች መሆኗ እየተነገረ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG