የኬንያ የሃገር ውስጥ ድርጅቶች ከለላ ካልተበጀላቸው አንድ ሺህ የሚሆኑ ድርጅቶችና አሥር ሺህ ሰዎች ሥራቸውን ሊነጠቁ እንደሚችሉ የሠራተኛ ማኅበራቱ አሳስበዋል።
ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ቀድም ብሎም ቢሆን ኬንያ ውስጥ ከመርከብ ላይ ዕቃ በማውረድና በማጓጓዝ ሥራ ላይ የተሠማሩ ድርጅቶች ከዓለምአቀፍ የመርከብ ድርጅቶች ፉክክር ገጥሟቸው ቆይቷል።
ጁማ ማጃንጋ ከሞምባሳ ያጠናቀረውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።