በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ፍቅረኛውን በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ኬንያ ውስጥ በድጋሚ ተያዘ


ፍቅረኛውን በመግደል የተጠረጠረው ኬቨን ካንጌቲ
ፍቅረኛውን በመግደል የተጠረጠረው ኬቨን ካንጌቲ

በአሜሪካ ፍቅረኛውን በመግደል ተጠርጥሮ፣ ኬንያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ከነበረበት እስር ቤት ባለፈው ሳምንት አምልጦ የነበረውን ግለሰብ መልሶ መያዙን የኬንያ ፖሊስ ዛሬ አስታውቋል።

ኬቨን ካንጌቲ ወደ አሜሪካ ለመተላለፍ ተይዞ ቆይቶበት ከነበረው እስር ቤት ባለፈው ሳምንት በማምለጡ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን ስቦ ነበር።

ባለፈው ዓመት፤ ማርግረት ምቢቱ የተባለች ግለሰብ፣ ባስተን በሚገኘው ሎጋን አየር ማረፊያ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ በስለት ተወግታ መኪና ውስጥ ሕይወቷ ካለፈ በኋላ መገኘቷን ተከትሎ፣ የአሜሪካና የኬንያ መርማሪዎች ግለሰቡን ለመያዝ አሰሳ ጀምረው ነበር።

ባለፈው ሳምንት ከእስር ማምለጡ፣ የኬንያን ፖሊስ ያስደነገጠ እና ያሳፈረ ጉዳይ እንደነበር አዛዡ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣ በኋላ ባለፈው ጥር በቁጥጥር ሥር የዋለው ኬቨን ካንጌቲ፣ ባለፈው ሳምንት ከተያዘበት አምልጦ፣ ናይሮቢ ዳርቻ ከሚገኙ ዘመዶቹ ቤት ተደብቆ እንደነበር ዘገባው አመልክቷል።

ከማምለጡ ጋር ተያይዞ አራት ፖሊሶች፣ ሁለት ዘመዶቹና ጠበቃው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG