ባለፈው የኬንያ ምርጫ መሸነፋቸው የተነገረው ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ውጤቱን ባለመቀበል ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቤት ብለዋል።
የአሁኑ አቤቱታ በኦዲንጋ የፖለቲካ ህይወት ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።
አንዳንድ ተቺዎች ‘ኦዲንጋ ሽንፈታቸውን መቀበል አይፈልጉም’ በሚል እየተሳለቁባቸው ቢሆንም የህግ ባለሙያዎች ግን የኦዲንጋ ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ ‘የኬንያን ምርጫ ተአማኒነትን ያሳድጋል፤ ለሃገሪቱ የተረጋጋ ዴሞክራሲም ይጠቅማል’ ይላሉ።
ጁማ ማጃንጋ ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።