በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦዲንጋ ፍርድ ቤት ሊሄዱ ነው


ስቴፋን ዱያሪች
ስቴፋን ዱያሪች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ወደ ኬንያ ደውለው ከተመራጩ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር መነጋገራቸውን ቃል አቀባያቸው ስቴፋን ዱያሪች ማምሻውን ኒው ዮርክ ላይ ለጋዜጠኞች ገለፁ።

ዋና ፀሃፊው ነገም በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ወቅት የሩቶ ተፎካካሪ የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ ዘንድ በተገኙ ጊዜ ደውለው እንደሚያነጋግሯቸው ዱያሪች አመልክተዋል።

ትናንት ውጤቱ በተነገረበት የኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸው የተገለፀው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል ለዳኛ አቤት እንደሚሉ አስታውቀዋል።

ዋና ፀሃፊ ጉቴሬሽ ኬንያዊያን ምርጫውን ያካሄዱበትን መንገድ ማድነቃቸውንና አጠቃላይ ሂደቱ ባሉት ህገ መንግሥታዊና የፍትህ ማዕቀፎች ውስጥ ፈጥኖ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ እንዳላቸው መግለፃቸውን ቃል አቀባያቸው ዱያሪች ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሣምንት የደረሰበት መጥፋቱ የተነገረ የኬንያ ምርጫ አስፈፃሚ ሞቶ መገኘቱን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

XS
SM
MD
LG