በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” የተባሉ 47 ሠዎች ሕይወታቸው አለፈ


“ኢየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” የተባሉ 47 ሠዎች ሕይወታቸው አለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:42 0:00

በአንድ ቤተ ክርስቲያን መሪ “ኢየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” ተብለው የተነገራቸው 47 ሠዎች ሞተው መገኘታቸውን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በቤተክርስቲያኑ መሪ ንብረት ላይ እንደነገሩ የተቀበሩ 26 አስከሬኖችን አንድ የፍለጋ ቡድን ትናንት እሁድ አግኝቷል፡፡

ማሊንዲ በተሰኘችውና በኬንያ ባህር ዳርቻ በምትገኝ ከተማ በቤተክርስቲያኑ መሪ፣ “ኢየሱስን እንድታገኙ ተራቡ” ተብለው የተነገራቸው አማኞች ለረጅም ግዜ ራሳቸውን በማስራባቸው ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ትናንት እሁድ ብቻ በተደረገ ፍለጋ እና ቁፋሮ 26 አስከሬኖች ሲገኙ፣ የአጠቃላይ ሟቾችን ቁጥር 47 አድርሶታል፡፡

ፖል ማከንዚ ተንጊ የተባሉት የ“መልካም ዜና ዓለም አቀፍ ቤ/ክርስቲያን” መሪ “ኢየሱስን ማግኘት የሚፈልግ አማኝ፣ ራሱን እስከ ሕይወት ፍጻሜ ካስራበ ያገኘዋል” ብለው አማኞችን በመስከባቸውና አንዳንዶቹም በማመናቸው በረሃብ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

የአፍሪካ ሰብዓዊ መብት ድርጅት ዲሬክተር የሆኑት ሁሴን ካሊድ፣ አንድ በሕይወት የተገኘች አማኝ አሁንም ምግብ ለመውሰድ ፈቃደኛ እንዳልሆነች ይናገራሉ፡፡

“ዛሬ አንድ በሕይወት የተረፈች የቤተክርስቲያኑ ተከታይ አግኝተን ነበር፣ ነገር ግን የመጀመሪያ ዕርዳታ ለማግኘትም ይሁን ምግብ ለመውሰድ አልፈለገችም፡፡ ምግብ ላለመውሰድ አፏን ግጥም አድርጋ ዘጋችው፡፡ እስከ ሞት ለመጾም ወስናለች፡፡ ይህ የችግሩን ክብደት ያሳያል” ብለዋል ካሊድ።

በዚህ የቤተ ክርስቲያኑ መሪ ባለቤት በሆኑበት ሥፍራ ተጨማሪ የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል መረጃ ፖሊስ አግኝቷል፡፡ ፖሊስ ባለፈው ሳምንት አሰሳ ባደረገበት ወቅት 15 እጅግ የተጎዱ ሰዎችን አግኝቶ ነበር፡፡ ከእነዛ ውስጥ አራቱ ሕይወታችው አልፏል፡፡

ሌሎች የቤተክርስቲያኑ ተከታዮች ተደብቀው ሊሆን ይችላል የሚል ፍራቻም አለ፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ መሪ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከሆኑ በኋላ ላለፉት አራት ቀናት የረሃብ አድማ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ከሕጻናት ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ሁለት ግዜ በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ሁለቱንም ግዜ በዋስትና ተለቀው በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ ነበሩ፡፡

XS
SM
MD
LG