No media source currently available
ኬንያ በቻይና ውሃን ግዛት በተቀሰቀሰው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ሀገር መመለስ ያልቻሉ ዜጎቿን ለመደጎም ገንዘብ መመደቧን ይፋ አድርጋለች። የኬንያ የጤና ሚኒስትር ዳይሬክተር ድጋፉ ለትምህርት ሄደው ቻይና ውሃን ግዛት የሚገኙ የሀገራችንን ዜጎች ለመርዳት የሚውል ነው ብለዋል።