በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይና የተገነባው የኬንያ ምድር ባቡርና የሞምባሳ ወደብ


ፎቶ ፋይል - የጭነት መኪናዎች ከኬንያ ዋና ከተማ ዳርቻ ከምትገኘው ሞምባሳ ወደብ አውራ ጎዳና ላይ ሲጓዙ
ፎቶ ፋይል - የጭነት መኪናዎች ከኬንያ ዋና ከተማ ዳርቻ ከምትገኘው ሞምባሳ ወደብ አውራ ጎዳና ላይ ሲጓዙ

አዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከመጀሪያዎቹ ሥራዎቻቸው ውስጥ፣ መርከቦች፣ በሞምባሳ ወደብ የሚገኙ የጭነት ኮንቴይነሮችን ወደ ዋና ከተማዪቱ ናይሮቢ ከማምጣት ይልቅ፣ እዚያው ወደቡ ላይ እንዲያራግፏቸው አዘዋል፡፡

ምንም እንኳ ተችዎች ይህ በሞምባሳ ወደብ ላይ መጨናነቅን ይፈጥራል ቢሉም፣ ሩቶ ግን በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ቃል የገቡትን ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኬንያ መንግሥት በ2011 ዓ.ም የጭነት ማራገፊያና መቆጣጠሪያ አገልግሎት ሥራውን ህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ከሚገኘው የኬንያው ሞምባሳ ወደብ፣ ናይሮቢና ኔቫሻ ወደ ተባሉ የመሃል አገር ከተሞች አዛውሯል፡፡

ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የአገልግሎት ሥራዎቹ ወደ ሞምባሳ እንዲመለሱ በዚህ ሳምንት ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

ለኬንያውያን ቃል በገባሁት መሰረት የተከማቹ ሸቀጦችን የሚያነሱና ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ወደ ሞምባሳ ለመመለስ የሚያስችሉ መመሪያዎችን አወጣለሁ፡፡ ይህ በሞምባሳ በሺዎች የሚቆጠሩ የሥራ እድሎችን ይፈጥራል፡፡

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ከቻይና በተገኘው የ4.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተሰራውን (Standard Gauge Railway SGR) የተባለውን የምድር ባቡር ጠቀሜታ ለማሳደግ፣ የጭነት ማራገፊያ አገልግሎቱን ወደ ናይሮቢ አዛውረውት ነበር፡፡ የኬንያ ባላሥልጣናት የብድር እዳውን ለመክፈል ጥሩ ዘዴ ነው ብለው የወሰኑት ውሳኔ፣ ኩባንያዎች ምድር ባቡሩን ለመጠቀም የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ አስገድዷል፡፡

ማከሰኞ የተላለፈውን የሩቶ ውሳኔ፣ “እዳ ለመክፈል ተብሎ የወደብ ከተማችን የንግድ ኢንቅስቃሴዎች መዘጋት የለበትም” የሚሉት የሞምባሳ ገዥ ሆነው አዲስ የተመረጡት አብዱልስዋማድ ሸሪፍ ናስር በደስታ ተቀብለውታል፡:

በቻይና የተገነባው የኬንያ ምድር ባቡርና የሞምባሳ ወደብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:45 0:00

ለረጀም ጊዜ ስንታገለው የቆየንበትና በግልጽ የተናገርነው ነገር ነው፡፡ የምድር ባቡር ጣቢያውን ዕዳ ለመክፈል እንኳ ቢያስፈልግ እዳውን መክፈል የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶች አሉ፡፡ የግድ የአገሪቱን አንድ የኢኮኖሚ ክፍል የሚገድል መሆን አይገባውም፡፡

በ2014 ዓ.ም በወጣው የኢኮኖሚ ጥናት SGR የተባለው የምድር ባቡር በ2013 ዓም የ22.6 ከመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ በ2012 ከነበረበት የ87 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ በማምጣት በ2013 ዓ.ም 108 ሚሊዮን ዶላር አስመዝግቧል፡፡ ጭማሪው የመጣው ወደ ናይሮቢ ከሚያመላልሰው የጭነት አገልግሎት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በብዙ ሰዎች ዘንድ የጭነት አገልግሎቱ ወደ ሞምባሳ መመለስ፣ የምድር ባቡሩን የሥራ እንቅስቃሴ የጭነት ተሽካርካሪ ኩባኒያዎች ስለሚወስዱት እዳውን ለመክፈል አዳጋች ያደርግበታል፣ በመጨረሻም የግንባታው ወጭ ግብር ከፋዮች ላይ ይወድቃል የሚል ሥጋት ማሳደሩ ተነግሯል፡፡

አንዳንድ የንግድ ሰዎች የሞምባሳ ወደብ በታሪኩ እቃ በማራገፍም ሆነ ጭነት ኮንቴይኖሮችን ለማጓጓዝ ዘገምተኛ መሆኑን በመግለጽ ይከራከራሉ፡፡

በናይሮቢ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ገሪሾን ኢኬራ የሞምባሳ ወደብ ተጨማሪ ኃላፊነቶቹን ሊወጣ እንደማይችል ይተነብያሉ፡፡

“በአጭር ጊዜ ውስጥ የጭነት ማጓጓዣዎቹ መዘግየት፣ ሌሎች ችግሮች የሚያስከትሉትን ጉዳትና የሞምባሳ ወደብ አውራ ጎዳናዎች መጨናነቅ፣ በየቦታው በፖሊስ ቢሮ ያለውን ሙስና ማስተዋል እንጀምራለን፡፡” ብለዋል ኢኬራ፡፡

የአስተዳደርና የከተማ ልማት ባለሙያው አልፍሬድ ኦሜንያ መንግሥት ወደቡን የሚያስተዳደሩ ጥሩ ሥራ አስኪያጆችን ከሾመ ችግሮቹ ሊወገዱ እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ይህኑንም ሲገልጹ

“ፕሬዚዳንቱ ትክክለኛውን ነገር ያደረጉ ይመስለኛል፡፡ ይህ ለጊዚያዊ የፖለቲካ ፍጆታ የተደረገ ሳይሆን በተቀናጀ እቅድ፣ በተቀናጀ ስትራቴጂና ከአገራችን ልማት ጋር የተቀናጀ እርምጃ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡” ብለዋል፡፡

ሁኔታው ዕጅግ ከፋ ቢባል በሞምባሳ ወደብ ያለው መጨናነቅና ሙስና፣ ከጎረቤት አገራት የሚመጡ ነጋዴዎች ወደ ሌሎች ወደቦች እንዲጎርፉ የሚያደርጋቸው ሲሆን፣ ኬንያም ለልማትም ሆነ እዳዋን ለመክፈል የሚያስፈልጋትን ገቢ እንድታጣ ሊያደርጋት ይችላል፡፡

XS
SM
MD
LG