No media source currently available
የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በመንግሥትና በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ስምምነት ያመጣል የተባለ ሰነድ ትናንት ይፋ አድርገዋል። በመጋቢት በተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋና በራሳቸው መካከል በተደረሰ ስምምነት መሠረት ሲዘጋጅ የቆየውን “ድልድዮችን መዘርጋት” ተብሎ የተሰየመ ሰነድ ኬንያታ ሲያጸድቁ የፖለቲካ መሪዎች ልዩነቶችን የሚያገዝፉ ጉዳዮችን ትተው በሚያስማሙ አጀንዳ ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ አቅርበዋል።