በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካ ነክ ርእሶች፡ በስደተኞች የተጨናነቀው ዳዳብ


አፍሪካ ነክ ርእሶች፡ በስደተኞች የተጨናነቀው ዳዳብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:55 0:00

የዛምቢያ የቀድሞ ፕሪዚዳንት ልጅና ባለቤታቸው ታሰሩ

ከሶማሊያ፣ በድርቁ እና በግጭቶች ምክንያት በብዛት የሚሰደዱ ሰዎች፣ ኬኒያ ወደሚገኘው የዳዳብ የስደተኛ መጠለያ ካምፕ እየጎረፉ ነው፡፡

ይኸው ስደት፣ ቀድሞውንም በተፈናቃዮች በተጨናነቀው ካምፕ የሚሰጠውን አገልግሎት ይብሱን አዳክሞ፣ በስደተኞቹ ጤና ላይ ከባድ አደጋ ደቅኗል፤ ሲሉ፣ የረድኤት ድርጅቶች አስጠንቅቀዋል፡፡

በሌላ ዘገባ ደግሞ፣ የዛምቢያ ፖሊሶች፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤድገር ሉንጉን ወንድ ልጅንና ባለቤታቸውን፣ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በቁጥጥር ሥር አውሎ በሙስና ወንጀል ክሥ መሥርቶባቸዋል፡፡ በሕገ ወጥ መንገድ ያገኙትን ገንዘብ፣ በሕጋዊ አካል በመደበቅ፣ እንዲሁም በወንጀል ተግባር በተገኘ ገንዘብ የተገዛ ከአምስት ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ንብረት ሰብስበዋል፤ ተብለው ተወንጅለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ፣ በቀጠሮ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

አገር ወዳድ ግንባር ፓርቲ የተባለው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ፓርቲ በበኩሉ፣ እስሩን፣ መንግሥት፥ በሉንጉ ቤተሰብ ላይ የቀጠለው የማሳደድ አድራጎት አካል ነው፤ በማለት ውንጀላውን አስተባብሏል፡፡

ጁማ ማጃንጋ ከዳዳብ ካምፕ ያጠናቀረውን ፣ ካቲ ሾርት ከዋና ከተማዋ ሉሳካ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ቆንጅት ታየ ለአፍሪካ ነክ ርእሶች አሰናድታዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG