ዋሺንግተን ዲሲ —
ካቡል ውስጥ በሚገኝ አንድ የሺዓይት ሙስሊሞች መስጂድ ላይ የደረሰ የአጥፍቶ ጠፊ ፍንዳታ፣ ሥድስት ሰዎች ገድሎ ሌሎች 27 ማቁሰሉን፣ የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የዓይን ምስክሮች እንደገለጹት፣ አጥቂው እረኛ መስሎ ሕዝብ ወደተሰበሰበበት ቃላእ ፋተሁላህ አካባቢ ወደሚገኘው መስጊድ እንደገባ፣ ፖሊሶች ተኩስ እንደከፈቱበት ነበር ፍንዳታውን ያደረሰው።
የሟቾች ቁጥር ባለሥልጣናት ከገለጹት ከፍ ሊል እንደሚችልና፣ ህፃናትም ሰለባዎች እንደነበሩ ታውቋል።
ፕሬዚደት አሻራፍ ጋኒ ጥቃቱን አውግዘው፣ ይህ ዓይነቱ ሽብር አፍጋኒስታንን እንደማይከፋፍላትም አመልክተዋል።
ታሊባን “በጥቃቱ እጄ የለበትም” ሲል አስተባብሏል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ