በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃገሮች የሁለቱን ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ሪፖርት ደገፉ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ)፣ በስሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ተፈጸመዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አስመልክቶ፣ ያደረጉትን የጋራ ምርመራና ግኝት፣ አስመልክቶ ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ 16 ሃገሮች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

የሃገራቱ መግለጫ “እኛ አውስትራሊያ፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣ ሉክዘምበርግ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኒውዚላንድ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ” እያለ በመዘርዘር፣ በሁለቱ ድርጅቶች የጋራ ሪፖርት ላይ የተጠቀሱትን ግኝቶች በመጥቀስ “ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን” ይላል፡፡

መግለጫው “የተባበሩት መንግሥታቱና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ እኤአ ከህዳር 3/2020 ጀምሮ እስከ ሰኔ 28/2021 ድረስ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ግጭት ተሳታፊ በሆኑ ሁሉም ወገኖች፣ የተፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ጥቃቶች፣ በከፍተኛ ደረጃ የተጣሱትን ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብትና ህግጋቶችን ለማጣራት በጋራ ያደረጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡” ብሏል፡፡

“በማጣራቱ ሂደት ሰነዶችን ተበዳዮችንና በደሉ የተፈጸመባቸውን አንዳንድ አካባቢዎች ዘንድ ለመድረስ ብርቱ ፈተና የነበረ ቢሆንም ሁሉቱ ድርጅቶች መረጃዎቾቹን በማግኘት ግልጽና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ምርመራቸውን አካሂደዋል” ሲል የአገራቱ መግለጫ ያመሰግናል፡፡

ሃገሮቹ በመግለጫቸው “የተደረጉ ዓለም አቀፋዊ የመብት ጥሰቶችና የተጣሱ ዓለም አቀፋዊ ህግጋትን በማሳየት ረገድ ሰነዶቹ የሚኖራቸው ጠቀሜታ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ሁሉ ፍትህ እንዲያገኙና ጥቃቱን ያደረሱትም ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋልም “ብለዋል፡፡

“በተለይም አሁንም የሰብዓዊ እርዳት ተደራሽነትን በመገደብ ረገድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት የተገለጸውን ስጋት እናጋራለን” ሲሉ አገሮቹ በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

በሪፖርቱ ውስጥ የተነሱ ውንጀላዎችና የተጠቀሱ ጥሰቶች ሁሉ አሁንም ተጫማሪ ምርመራን የሚጠይቁ መሆኑን እንደሚያሳይ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑን ሁሉም ወገኖች በሪፖርቱ የተጠቀሱትን ምክሮች እንዲቀበሉና ተግባራዊ እንዲያደርጉም የሚያበረታቱ መሆኑን አገሮቹ በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ መንግሥት በሪፖርቱ ውስጥ ለተጠቀሱት ነገሮች ምላሽ ለመሰጠት ያለውን ቁርጠኝነት እንገነዘባለን” ያለው መግለጫ የኤርትራ መንግሥትና ህወሃትና በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እናሳስባለን ብሏል፡፡

በሪፖርቱ የተነሱ ጥሰቶች ጦርነት፣ ተባብሶ እየቀጠለ ባለበት ባሁኑ ወቅትም የቀጠሉ መሆኑን መግለጫው ጠቅሶ፣ በዚያ መጠንም በረሀብና በጦርነት በሰዎች ላይ የሚደርሰው እልቂትም እየጨመረ እንደሚሄድ የሪፖርቱ ግኝቶች በማሻያማ መልኩ በግልጽ ያመለከታሉ ብሏል፡፡

የአገራቱ በመግለጫቸው “የኢትዮጵያን መረጋጋትና ሉአላዊና የወሰን አድንድነት እናከበራለን” ብለዋል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ተወካዮችና እና ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ግጭቱ አብቅቶ ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን በሚያመጡ ጉዳዮች አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG