በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ እና የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ


የተመድ እና የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የሴኩሪቲ የጋራ ግብረ ኃይል ባለፈው ማስከኞ 16ኛ ተከታታይ የምክክር ስብሰባዎቻቸውን አዲስ አበባ ውስጥ አካሄዱ።

ስብሰባው በተመድ እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል ያለውን ወዳጅነት የመረመረ ከመሆኑም በላይ፣ ይህ የጋራ ግብረ ኃይል በተለይም ሁለተኛው ዓመታዊ የተመድ እና የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚካሄድ የደረሰበትን ሥምምነት ጨምሮ፣ በተመድ እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል ያለው ወዳጅነት ያስመዘገባቸውን ፍሬያማ ውጤቶችም አድንቋል።

በአፍሪካ አገሮች በሚካሄዱ ምርጫዎች ሊኖር የሚገባውን ትብብር ያጤነው ይህ ጉባዔ፣ በቡርኪና ፋሶ እና በኒዠር ያለውን የደኅንነት ሁኔታ ጨምሮ፣ ስለ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ፣ ስለማዕከላዊ አፍሪካ ሪፖብሊክ፣ ስለ ቡሩንዲ፣ ስለ ማሊ እና ስለ ሳህል ክልል ሴኩሪቲም አንስቶ ተወያይቷል።

ሊብያ፣ ደቡብ ሱዳንና ቻድ ተፋሰስ ሀይቅ ያለው ሁኔታም ተነስቶ ውይይት ተካሂዶበታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG