በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያና ዩክሬንን ውዝግብ ለማርገብ ዓለማቀፉ ጥረት ቀጥሏል


የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኪየቭ፥ የክሬን የሚገኘውን የቅዱስ ሶፊያ ካቴድራል ሲጎበኙ፣ እአአ ፌብሩዋሪ 1/2022
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኪየቭ፥ የክሬን የሚገኘውን የቅዱስ ሶፊያ ካቴድራል ሲጎበኙ፣ እአአ ፌብሩዋሪ 1/2022

ቀናትን ያስቆጠረውን የሩሲያና ዩክሬንን ውዝግብ እልባት ለመስጠት በየአቅጣጫው የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት መቀጠሉ ተመልክቷል፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ፑትን ጋር ዛሬ ረቡዕ በስልክ ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ተነግሯል፡፡

ጆንሰን የሩሲያና ዩክሬን ፍጥጫ በዲፕሎማሲው መንገድ ይፈታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ዩክሬን ራሷን የመከላከል መብት ያላት መሆኑንም የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያከማቸችው 100 ሺህ ጦር “በህይወታችን ሙሉ ያየነው ትልቁ የጸብ አጫሪነት የተገለጸበት ሳይሆን አይቀርም” ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የቱርክ ፕሬዚዳንት ታይፔ ኤርዶጋን ነገ ሀሙስ በዩክሬን ተገኝተው የዲፕሎማሲ መፍትሄ ለመሻት ወደ ኪየቭ እንደሚጓዙ ተዘግቧል፡፡

የሩሲያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት በሰጡት መግለጫ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ተባባሪዎችዋ፣ ዩክሬን የኔቶ ወታደራዊ ህብረት አባል እንዳትሆን፣ ሩሲያ ያቀረበችውን ከፍተኛ የደህንነት ጥያቄ፣ ችላ ብለውታል ብለዋል፡፡

የዩናዩትድ ስቴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን፣ ከሩሲያ አቻቸው ጋር ባደረጉት የስልክ ልውውጥ፣ ሩሲያ ውጥረቱን ለማርገብ ወታደሮችዋን በአስቸኳይ ከአካባቢው እንድታስወጣ አሳስበዋል፡፡

እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ግምት ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያሰፈረቸውን ጦር በመጨመር 127ሺ ማድረሷ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG