በሌላ በኩል የጅንካ ከተማ ነዋሪዎች፤ “በወንጀሉ ተሳትፎ የሌላቸው ወጣቶች እየታፈሱ ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሎጂ መምሕርና የሕግ እና የብዛሃነት ተመራማሪ ዶ/ር ኬሬዲን ተዘራ በደቡብ ክልል የማያባራ ተመሳሳይ ጥያቄዎች እየተነሱ የፀጥታ እና የሁከት ምንጭ የሚሆኑት በሕገመንግሥቱ ክፍተት እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በአግባባዊ በውይይት ይመለሳሉ የሚል ባህል እየጥፋ በመሆኑ ነው ብለዋል።