በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጅማ አይሮፕላን ጣቢያ ተከፈተ


ጅማ አባጅፋር ኤርፖርት
ጅማ አባጅፋር ኤርፖርት

የጅማ የአይሮፕላን ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዛሬ፤ ማክሰኞ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:16:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የጅማ የአይሮፕላን ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዛሬ፤ ማክሰኞ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

ጅማ አባጅፋር ኤርፖርትን መርቀው የከፈቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በከተማይቱ ውስጥ ወደፊት የሚገነባ የኢንዱስትሪ ዞን የመሠረት ድንጋይም አኑረዋል፡፡ የጅማ-ቦንጋን የ110 ኪ.ሜ አስፋልት መንገድም መርቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት ባለፉት 2 ሣምንታት በርካታ የመሠረተ-ልማትና የህዝብ አገልግሎቶችን ሲመርቁ ሰንብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅማ ከተማ ውስጥ መርቀው የከፈቷቸው የመጓጓዣ መሠረተ ልማት ተቋማት ወደ 1 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ መዋዕለ-ነዋይ የፈሰሰባቸው መሆናቸውን መንግሥቱ አስታውቋል፡፡

በ1956 ዓ.ም ሥራ የጀመረው ጅማ አባጅፋር አይሮፕላን ጣቢያ ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ወጥቶበት የተሠራ ትላልቅ አይሮፕላኖችን ማሣረፍ የሚያስችል ብቃት ያለው መሆኑንና በአንድ ጊዜ መንገደኞችን የመቀበልና የመሸኘት አቅሙን ከሦስት እጥፍ በላይ መጨመሩን የመንግስቱ መረጃ ጠቁሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስት ኃይለማርያም ደሣለኝ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመጓዝ የምረቃ መቀነቶችን ሲቆርጡና የመሠረት ድንጋይ ሲያኖሩ ነው ይሰነበቱት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG