በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣሊያን የጠረፍ ጠባቂዎች 700 ፍልሰተኞችን ከሞት ታደጉ

ትናንት ረቡዕ በሲሲሊው ካታኒያ ወደብ በአገልግሎት ብዛት አርጅቶ ከዛገው ጀልባ ውስጥ የጣልያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ከሞት ያዳኗቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ደስታቸውን ሲገልጹ ታይቷል፡፡

ነዳጅ አልቆባት ባህር ላይ ቆማ በነበረችው ጀልባ ውስጥ 700 የሚደርሱ ፍልሰተኞች እንደነበሩ ተነግሯል፡፡

በዚህ የአውሮፓውያኑ 2023 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ በአፍሪካና አውሮፓ ደቡባዊ የባህር ዳርቻዎች ባለው አደገኛ የባህር መስመር ላይ 441 ፍስልተኞች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ለብዙዎቹ ፍልስተኞች ሞት አስተዋጽኦ ያደረገው “በመንግሥት የሚመራው የነፍስ አድን ሥራ መዘግየቱ” እንደሆነ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ትናንት ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

የጣልያን ቀኝ ክንፍ መንግሥት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን ፍልሰተኞች ብዛትና ሞት ለመታደግ ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ለስድስት ወራት የሚቆይ ብሄራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቷል፡፡ ከዚሁ በተያያዘ የጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ መሎኒ እና ካቢኔያቸው የ5 ሚሊዮን ዩሮ (5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር) ወጪ ፈቅዷል፡፡

ይህ የአውሮፓውያን ዓመት ከገባ ወዲህ የጣልያን ወታደራዊ ጀልባዎች ወይም የበጎ አድራጎት መርከቦች ባህሩ ላይ የደረሱላቸው ወይም ካለምንም ዕርዳታ የደረሱ 31 ሺ ፍልሰተኞች ጣሊያን መግባታቸውን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG