በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጣልያን ፍርድ ቤት ለግራዚያኒ ሃውልት ያቆሙትን በእስራት ቀጣ


Marshal Graziani
Marshal Graziani

እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2012 ከሮም ከተማ በስተ ምሥራቅ ሃምሳ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምትገኘው የአፊሌ ከተማ “አባትነት” እና “ክብር” የሚሉ መጠሪያዎች ተሰጥተውት በ160 ሺህ ዶላር ወጪ ለግራዚያኒ ባቆሙት የመታሰቢያ ሃውልት የከተማይቱ ከንቲባ ኤርኮሌ ቪሪ የስምንት ወር ሁለቱ የምክር ቤቱ አባላት ጊያምፔሮ ፍሮሶኒ እና ሎሬንዞ ፔፐሮን እያንዳንዳቸው የስድስት-የስድስት ወራት እስር ተፈርዶባቸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ አሥር ሺዎች የተቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመርዝ ጋዝ የተገደሉበትን ጨምሮ በኢትዮጵያና በሊቢያ በፋሺስት ወረራ ዘመን በፈጸመው በርካታ የጦር ወንጀሎች ተጠያቂ ለሆነው ለሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰቢያ ሃውልት መቆሙን እና የመዝናኛ ሥፍራ ለክብሩ መሰየሙን በመቃወም ከሌሎች መሠረታቸው ጣልያን ከሆኑ ቡድኖች ጋር ላለፉት አምስት ዓመታት ከታገሉ ወገኖች አንዱ ነው። “ዓለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ - የኢትዮጵያ ጉዳይ” የኢትዮጵያውያን ማሕበር ይባላል።

ዜናውን ተከትሎ ከዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኪዳኔ ዓለማየሁ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።

የግራዚያኒ መታሰቢያ ሃውልት እና የጣልያኑ ፍርድ ቤት ውሳኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG