በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጣሊያን በአንድ የፍልሰተኞች ማቆያ ማእከል የተፈጠረ ሁከት ሳቢያ 14 ሰዎችን አሰረች


የፖንቴ ጋሌሪያ የፍልሰተኞች ማቆያ ማዕከል ሮም፣ ጣሊያን፤ እአአ ግንቦት 6/2017
የፖንቴ ጋሌሪያ የፍልሰተኞች ማቆያ ማዕከል ሮም፣ ጣሊያን፤ እአአ ግንቦት 6/2017

ሮም አቅራቢያ በሚገኝ አንድ የፍልሰተኞች ማቆያ ማእከል ውስጥ አንድ ወጣት ራሱን ካጠፋ በኋላ የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ የጣሊያን ሕግ አስከባሪዎች 14 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ትላንት አስታወቁ።

ፍልሰተኞቹ ከትላንት በስቲያ እሁድ ጥር 26, 2016 ዓም የነበሩትን የማቆያ ሥፍራ በኃይል ጥሰው በመውጣት፡ ወደ አንድ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ሥፍራ በመማምራት፣ የመኝታ ፍራሾችን ማቃጠል እና ቁሳቁሶችን መወርወር በጀመሩበት ወቅት ሁለት ፖሊሶች እና አንድ ወታደር የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው መሆኑም ተዘግቧል።

ፖሊስ ከ’ፊቺሚኖ ከተማ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኝ ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ስደተኞች ለአጭር ጊዜ የሚቆዩበትን የፖንቴ ጋሌሪያ ማዕከልን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG