በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ካቢኔ አክራሪ ብሄርተኛ አባል የእየሩሳሌም ጉብኝት


ፎቶ ፋይል፦ ኢታማር ቤን ጊቪር
ፎቶ ፋይል፦ ኢታማር ቤን ጊቪር

በእስራኤል በአዲሱ ቀኝ እክራሪው የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መንግሥት የካቢኔ ሚንስትር የሆኑ አክራሪ ብሄርተኛ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደጋጋሚ ግጭት የሚከሰትበትን የእየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራ ጎበኙ። የሚንስትሩን ጉብኝት ፍልስጥኤማውያን "ጠብ ፈላጊነት" ብለውታል።

ኢታማር ቤን ጊቪር ዛሬ ማክሰኞ ብዛት ባላቸው ፖሊሶች ታጅበው በአይሁድ ዘንድ ቴምፕል ማውንት ቤተ መቅደስ ሙስሊሞች ደግሞ የአል አቅሳ መስጂድ ግቢ ብለው የሚጠሩት ስፍራ ገብተዋል።

በተያያዘ ዜና ዛሬ ቀደም ብሎ በዌስት ባንኩዋ ቤተልሄም ከተማ አቅራቢያ አንድ የአስራ አምስት ዓመት ወጣት በእስራኤል ወታደሮች ተተኩሶበት ተገድሏል።

የእስራኤል የጦር ኃይል በጉዳዩ ላይ አስተያየት አልሰጠም።

XS
SM
MD
LG