በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በአዲሱ ዓመት በጋዛ በአካሄደችው ጥቃት 12 ሰዎች ሞቱ


እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ በአካሔደችው ጥቃት ከተማው በጭስ ተሸፎኖ ይታያል፡፡
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ በአካሔደችው ጥቃት ከተማው በጭስ ተሸፎኖ ይታያል፡፡

እስራኤል ዛሬ ረቡዕ በጋዛ ሰርጥ በአካሔደችው ጥቃት ቢያንስ 12 ፍልስጤማውያን መሞታቸውን እና አብዛኞቹ ሴቶች እና ሕፃናት መሆናቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ወደ 15 ወራት የሚጠጋ ጊዜ ያስቆጠረው ጦርነትም ምንም የማብቂያ ምልክት ሳያሳይ ወደ አዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት ተሸጋግሯል።

የእስራኤል አንደኛው ጥቃት በሰሜናዊ ጋዛ ውስ፣ ጃባሊያ በተባለ እና እስራኤል ጥቃት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በአካሔደችው ዘመቻ ከፍተኛ ውድመት በደረሰበት አካባቢ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ አርፏል። በቤቱ ውስጥ የነበሩ አንድ ሴት እና ስድስት ሕፃናትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ ከ12 በላይ የሚኾኑ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በመካከለኛው ጋዛ በሚገኝ ቡሬይጅ የተባለ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ ማምሻውን በተፈፀመ ሌላ ጥቃት ደግሞ አንድ ሴት እና አንድ ሕፃን መገደላቸውን አስክሬናቸውን የተረከበው አል-አቅሳ ሆስፒታል አመልክቷል።

እስራኤል በአካባቢው ጥቃት ያካሔደችው የፍልስጤም ታጣቂዎች በቅርቡ ከአካባቢው የተነሳ ሮኬት በመተኮሳቸው ነው ብላለች።

እስራኤል ከዓመት በላይ በአካሔደችው ጥቃት የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ45 ሺሕ ማለፉን የጋዛ ጤና ሚኒስትር ያስታወቀ ሲሆን፣ እስራኤል በጥቃት ለሞቱ ሲቪሎች ተጠያቂ የምታደርገው ሐማስን ነው። እስከ አኹን በአካሔደችው ዘመቻም 17 ሺሕ የፍልስጤም ታጣቂዎችን መግደሏን ትገልጻለች።

በጋዛ ከዓመት በላይ የተካሄደው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት ያስከተለ ሲሆን፣ ከ2.3 ሚሊየን በላይ ከሚሆነው የጋዛ ነዋሪ 90 ከመቶ የሚሆነው ከመኖሪያ ቤቱ ተፈናቅሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG