በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የጦር ካቢኔያቸውን በተኑ


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ዛሬ ሰኞ የጦር ካቢኔያቸውን መበተናቸውን፣ አንድ የእስራኤል ባለሥልጣን አስታወቁ።

ውሳኔው የተላለፈው፣ የቀድሞ ጀነራል ቤኒ ጋንትዝ፣ ባለፈው ሳምንት ድንገት ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ነው። ጋንትዝ፣ የኔታኒያሁን ጥምር መንግሥት የተቀላቀሉት፣ ጦርነቱ በጀመረበት ጥቅምት ወር ላይ ሲኾን፣ የጦር ካቢኔው እንዲቋቋም ግፊት አድርገው ነበር። አሁን ጋንትዝ መልቀቃቸውን ተከትሎ፣ ኔታንያሁ ቡድኑን ለመበተን መገደዳቸው ተገልጿል።

የእስራኤል ጦር፣ በረኀብ ለተጠቁ ፍልስጥኤማውያን ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ ለማገዝ፣ በደቡባዊ ጋዛ በሐማስ ታጣቂዎች ላይ የሚያካሒደውን የቦምብ ድብደባ ለ11 ሰዓታት እንደሚያቆም አስታውቆ ነበር፡፡ ዛሬ ሰኞ፣ አልፎ አልፎ ከተከሠቱ ግጭቶች ውጭ፣ ውሳኔው ተግባራዊ መኾኑን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አመልክቷል።

እስራኤል፣ በደቡባዊ ጋዛ የምትፈጽመውን ጥቃት ለጥቂት ጊዜ እንደምታቆምና የርዳታ መኪናዎች በእስራኤል ቁጥጥር ሥር በሚገኘው ኬረም ሻሎም በተሰኘ መሸጋገሪያ በኩል እንዲገቡ እንደምትፈቅድ አስታውቃለች። የጭነት መኪናዎቹ፥ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ትልቅ አውራ ጎዳና ተጉዘው ምግብ እና የሕክምና አቅርቦቶችን ወደተለያዩ የጋዛ ክፍሎች እንዲደርስ ያደርጋሉ፤ ተብሎ ይጠበቃል።

ኾኖም፣ የእስራኤል ጦር፥ በታላላቅ አውራ ጎዳናዎች ላይ ለሚጓዙት የርዳታ መኪናዎች ጥበቃ ያደርግ እንደኾን፣ እስከ አሁን የተገለጸ ነገር የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG