በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ደማስቆን ከአየር ደበደበች


የእስራኤል የአየር ጥቃት በደረሰበት የደህንነት መኮንኖች እና የነፍስ አድን ሰራተኞች በሥራ ላይ፣ በደማስቆ፣ ሶሪያ
የእስራኤል የአየር ጥቃት በደረሰበት የደህንነት መኮንኖች እና የነፍስ አድን ሰራተኞች በሥራ ላይ፣ በደማስቆ፣ ሶሪያ

እስራኤል በሶሪያ መዲና ደማስቆ ሁለት ሥፍራዎችን ከአየር መደብደቧን የሶሪያ መንግሥት የዜና አገልግሎት አስታውቋል።

በድብደባው 15 ሰዎች ተገድለዋል። ሌሎች 16 ሰዎች መጎዳታቸውንም ዜና አገልግሎቱ አስታውቋል።

በጥቃቱ አንዱ ኢላማ የነበረው 'እስላማዊ ጂሃድ’ የተሰኘ የፍልስጤማውያን ቡድን ይጠቀምበት የነበረ ቢሮ መሆኑ ታውቋል።

ማዘኽ እና ኩድሳያ በተሰኙ ሥፍራዎች የሚገኙ ሁለት ሕንጻዎች የአየር ጥቃት ደርሶባቸዋል።

ማዘኽ በተሰኘው ሥፍራ የሚገኝ ባለ 5 ፎቅ ሕንጻ በሚሳይል ተመትቶ ፈርሶ ማየቱን የአሶሲዬትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ ከሥፍራው ዘግቧል።

የእስራኤል ሠራዊት “ሽብርተኛ” ሲል በጠራው ድርጅትና አባላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።

‘እስላማዊ ጂሃድ’ የተሰኘው ቡድን ባለፈው ዓመት እ.አ.አ የጥቅምት 7 ቀን በእስራኤል ላይ ጥቃት በተሰነዘረበት ወቅት ተሳታፊ ነበር ሲል የእስራኤል ሠራዊት ያስታውቃል። በጥቃቱ 1ሺሕ 200 ሰዎች ሲገደሉ 250 የሚሆኑ ደግሞ ታግተው ወደ ጋዛ ተወስደው ነበር።

ሠራዊቱ አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኘው በ ‘እስላማዊ ጂሃድ’ ላይ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።

እስራኤል ጋዛ ላይ ባደረሰችው ጥቃት እስከ አሁን በአብዛኛው ሴቶች እና ሕፃናት ጨምሮ ከ43 ሺሕ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤማውያኑ የጤና ባለሥልጣናት ያስታውቃሉ። ባለሥልጣናቱ በሚሰጧቸው አሐዞች ተዋጊዎችንና ሲቪሎችን ለይተው እንደማያቀርቡ የአሶሶዬትድ ፕረስ ዘገባ አያይዞ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG