በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በኬንያ ጉብኝት ላይ ናቸዉ


በትላንት ናይሮቢ የገቡት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዛሬ ጠዋት ከኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በኬንያ ቤተ መንግሥት ዉይይት አድርገዋል።ከዉይይታቸዉ በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ ሁለቱ ሃገሮች በተለያዩ መስኮች ስምምነት መፈራረማቸዉን ይፋ አድርገዋል። ፕሬዝደንት ኡሁሩ ስለ ስምምነቱ ዝርዝር ተጠይቀዉ ስምምነቶቹ በግብርናና በፀጥታ ዙርያ መሆኑን አሳዉቀዋል።

ኬንያ ውስጥ የሦስት ቀናት ጉብኝት በማካሄድ ላይ የሚገኙት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከኬንያው ፕረዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ መሰረት በፀጥታና በግብርና መስክ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራርመዋል ሆኖም የስምምነቱ ይዘት በይፋ አልተገለፀም።

የኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሃገራቸዉ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሃገሮች እስራኤል በውሃ አጠቃቀም እና በቴክኖሎጂ ክህሎት ያላትን እዉቀት መጋራት እንደሚፈልጉ ጠቅሰዉ ኬንያ ዜጎቿን ወዴ እስራኤል በመላክ በማስተማር ላይ እንደሚትገኝም ተናግረዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በበኩላቸዉ ሃገራቸዉ የቅድመ ስለላ ሥራ በማከናወን ብዙ የሽብር ጥቃቶችን ያከሸፈች ሃገር በመሆኗ ይህንን ክህሎት ለኬንያና ለሌሎች አፍሪካ ሃገሮች ማካፈል እንደሚትፈልግ ገልፀዋል።

በዩጋንዳ የአፍሪካ ጉብኝታቸዉን የጀመሩት ኔታንያሁ ከኬንያ በመቀጠል በሩዋንዳ እና ኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG