በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይሲል፣ አል-ባግዳዲ፡ እሥልምናና ጂሃዳዊያን


አይሲል የከሊፋ መንግሥቴን እደነግግበታለሁ የሚለው የኢራቅና የሶሪያ ክልል
አይሲል የከሊፋ መንግሥቴን እደነግግበታለሁ የሚለው የኢራቅና የሶሪያ ክልል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዓለምን የናጠ የሃያ ደቂቃዎች ስብከት ባለፈው ሐምሌ በኢራቂቱ ሞሱል ታላቁ መስጅድ ተሰማ፤ ድፍን ዓለምን ነጥጥ ውስጥ የከተተ፡፡

በማንኛውም መለኪያ - ይላሉ ዛሬ ተንታኞች ስለዚያ እጅግ ደፋር የተባለ ዲስኩር ስናገሩ - ደግሞም በራሱ በእሥልምና ውስጥ በጥባጭና ግልበጣ ጠንሳሽም ነበር፡፡ መላ መካከለኛ ምሥራቅን ወደ ብዙ ደም አፍሳሽ ነውጥና ሽብር ይዞት ዘቀጠ፡፡

እራሱን ከአል-ቃይዳ ገንጥሎ የወጣውና ‘እሥላማዊ መንግሥት ነኝ’ ያለው አንጁ መሪ አቡ ባክር አል-ባግዳዲ ካሊፌቱን ወይም የከሊፋ ግዛቱን ያወጀ ጊዜ የተከበሩና ፀንተው የኖሩ የሙስሊሙን ዓለም መሪዎች ምዕራቡንና መሰል ጂሃዳዊያንንም ለግልፅ ጠብና ግብግብ መጥራቱ ነበር፤ ‘ይዋጣልን’ ዓይነት፡፡

በኢራቅ ሰማዮች ላይ የአሜሪካ የጦር ድሮኖች እያንዣበቡ ባሉበት የፍልሚያ አውድ ውስጥ ‘ከየት መጣ? ምን ያስባል? ምን ይፈጥር ይሆን?’ የማይባለው የ42 ዓመት ዕድሜው አል ባግዳዲ “ከሊፋ ኢብራሂም ነኝ” አለና በዓለም ዙሪያ ያሉ አንድ ቢሊዮን ሙስሊሞች እርሱን ይከተሉ፣ እርሱ ይመራቸው ዘንድ ደነገገ፡፡

አል-ባግዳዲ ‘የዓለም ሙስሊሞች መሪ ነኝ’ ማለቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ አዋጁ ከጥቀት ወራት በፊት በስልቶች ወይም ስትራተጂ ጉዳይ ላይ መግባባት ተስኗቸው እና በእርሱም አልታዘዝ ባይነት ተጣልተው ጥሎት የሄደው አል-ቃይዳም ለእርሱ እንዲንበረከክ ፣ ለእርሱ እንዲገዛ ትዕዛዝ ማውጣቱ ነበር፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG