በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ቁጥር አንድ አሸባሪና የዋነኛው ጽንፈኛ ቡድን መሪ ተገደለ


"የአሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ኃይሎች ትላንት ለሊት በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ቆራጥንነት የተመላና እጅግ አደገኛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አካሂደው ተልዕኳቸውን በድል አጠናቀዋል።” የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ።

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ወታደራዊ ኃይል በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ባካሄደው ወታደራዊ ኦፕሬሽን ራሱን “እስላማዊ መንግስት” እያለ የሚጠራውን አሸባሪ ቡድን መሪ አቡበከር አል-ባግዳዲን “በማስወገድ” ከፍተኛ ብቃት የታየበት ዘመቻ አጠናቀቀ” ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ማለዳ ላይ ለአሜሪካ ሕዝብ በቴሌቭዥን ባሰሙት ንግግር አስታወቁ ፡፡

“ትናንት ምሽት አሜሪካ የዓለማችንን ቁጥር አንድ የአሸባሪዎች መሪ ለፍርድ አቀረበች። አቡ ባከር አል-ባግዳዲ ተገደለ፡፡

በዓለም የመጨረሻው ጨካኝ እና አሰቃቂ የሽብር ምግባሩ የታወቀው አይሲስ መስራች እና መሪ ነበር፡፡

አሜሪካ በሕይወት እጁን ለመያዝ አለያም ለመግደል ለበርካታ ዓመታት ስታድነው የቆየችው ባግዳዲ - በደህነት አደጋ ደቃኝነታቸው አስተዳደሬ ከሚፈልጋቸው ግለሰቦች ዋናውና ግንባር ቀደሙ ነበር። የአሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ኃይሎች ትላንት ለሊት በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ቆራጥንነት የተመላና እጅግ አደገኛወታደራዊ ኦፕሬሽን አካሂደው ተልዕኳቸውን በድል አጠናቀዋል።” ነበር ያሉት።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አክለውም አልባግዳዲ የታጠቀውን ፈንጂ ባፈነዳበት ወቅት የመሸገበት መተላለፊያ መደርመሱን ገልጠዋል። ባግዳዲ ባፈነዳው ፈንጂ የሦስት ልጆቹንም ሕይወት እንዳጠፋ ትራምፕ ተናግረዋል።

ስለ አሟምሟቱም ሲናገሩ “እንደ ውሻ .. እንደ ከሃዲ ሞተ።” ነው ያሉት።

ቁጥራቸው የበዛ የአልባግዳዲ ተዋጊዎች ሲገደሉና ሲማረኩ በዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች በኩል የሞተ ያለመንኖሩን ነው የተናገሩት።

ከዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ወታደራዊ ኃይል ጋር በሥፍራው በነበሩ ባለሞያዎች በባግዳዲዲ አስከሬን ላይ በተካሄደ የዲ ኤን ኤ ምርምመራ በእርግጥ የተገደለው አልባግዳዲ መሆኑን መረጋገጡን ትራምፕ አመልክተዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዓለም ቁጥር አንድ አሸባሪና የዋነኛው ጽንፈኛ ቡድን መሪ ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:02 0:00



የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG