በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራቅ በተቃውሞ ሰልፎችና የተያያዥ ግጭቶችን ሁኔታ ፕሬዚዳንቱ አወገዙ


የኢራቅ ፕሬዚዳንት ባራሃም ሳልህ
የኢራቅ ፕሬዚዳንት ባራሃም ሳልህ

የኢራቅ ፕሬዚዳንት ባራሃም ሳልህ በመንግሥት ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና በመገናኛ ብዙሃን አባላት ላይ የደረሱትን ጥቃቶች አወገዙ።

ሳምንቱን በተቃውሞ ሰልፎችና በተያያዥ ግጭቶች ላይ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ ስድስት ሺህ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

ጥቃቱን የፈፀሙትን ወንጀለኞችና ጠላቶች ሲሉ የጠሯቸው ፕሬዚዳንቱ ግጭቱ እንዲገታ ተማፅኖ አቅርበዋል።

ሳልህ በቴለቭዥን ለመላ ሃገሪቱ በተላለፈው ንግግራቸው ሃገራችን፣ ያለፈችበት ውድመት፣ ደም መፋሰስ፣ ጦርነት እና ሽብርተኝነት ይበቃታል ብለዋል።

ትናንት የሀገሪቱ የጦር ሰራዊት በባግዳድ ሳድር ቀበሌ በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀሙን አምኗል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG