ዋሺንግተን ዲሲ —
ዋና ጽ/ቤቱን ፓሪስ ያደረገው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ትላንት ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ፣ ኢራን ደረጃዋ ከቀድሞ በ6 ወርዶ ከ180 ሃገሮች አሁን 170ኛ ቦታ ላይ ትገኛለች ብሏል።
ኢራን እአአ በ2018 ደረጃዋ ወደ ግርጌ ሊወርድ የቻለውም በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ የሚጠቀሙ ባለሞያና አማተር ጋዜጠኞችን በብዛት ይዛ በማሠሯ መሆኑ ተመልክቷል።
ለጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ቡድን ያወጣው ሪፖርት አክሎም ኢራን በዓለም ጋዜጠኞችን በብዛት ከሚያስሩ ሃገሮች አንዷ ናት ብሏል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ