በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦማን ባህረ ሰላጤ ጥቃት የደረሰባቸው ሁለት መርከቦች ሁኔታ


አንድ የኢራን የጥበቃ ጀልባ ጥቃት ከደረሰባቸው ሁለት ነዳጅ ዘይት ተሸካሚ መርከቦች ከአንደኛው ያልፈነዳ ፈንጂን ሲያነሳ ያሳያል ያለውን ቪድዮ የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል ይፋ አድርጓል።

ሁለቱ መርከቦች በኦማን ባህረ ሰላጤ ጥቃት የደረሰባቸው ትላንት ነበር። አንደኛው መርከብ የኖርዌ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የጃፓኑ ኮኩካ ሳንዮ የመርከብ ኩባንያ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ያወጣቸው ምስሎች ደግሞ የተነሳው ፈንጂ ከጃፓኑ ነዳጅ ዘይት ተሸካሚ መርከብ ጋር ተያይዞ እንደነበር ያሳያሉ፤ የኖርዌዩ መርከብ በእሳት ጋይቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG