በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለማቀፉ የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ሰሜን ኮሪያን ይጎበኛሉ


ዓለማቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባች
ዓለማቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባች

ደቡብ ኮሪያ የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድር በኋላ፣ ሰሜን ኮሪያን እንደሚጎበኙ፣ ዓለማቀፉ የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ዛሬ ሰኞ አስታወቀ።

ኦሎምፒክስ ኃላፊ ቶማስ ባች በደቡብ ኮሪያዋ ፒዮንግቻንግ ከተካሄደው የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድር በኋላ፣ ሰሜን ኮሪያን እንደሚጎበኙ፣ ዓለማቀፉ የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ዛሬ ሰኞ አስታወቀ።

የዓለማቀፉ ኦሎምፒክስ ቃል-አቀባይ ማርክ አዳምስ እንዳሉት፣ ግብዣው የቀረበላቸው ከሰሜን ኮሪያ ሲሆን፣ ይህም ሁለቱ ኮሪያዎች በክረምቱ ኦሎምፒክስ ይካፈሉ እንደሆን ዓለማቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ባነጋገራቸውና ሰሜን ኮሪያም እንደምትካፈል ባረጋገጠችበት ውይይት ላይ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሰሜን ኮሪያ የክረምቱን ኦሎምፒክስ ውድድር ለፖለቲካ ጠቀሜታ ታውለው ይሆናል የተባለውን ወሬ አስተባብለዋል።

ዛሬ ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ ምንም እንኳ በሁለቱ መካከል የፖለቲካ ፍጥጫ መኖሩ ባይካድም፣ ሰሜን ኮሪያ ግን ይህን ውድድር በፍፁም ስፖርታዊ ስሜት ነው የተቀበለችው ሲሉ ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG