በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የለንደኑ ጉባኤ


አቶ ተሻገር አበራ እና አቶ ጃዋር መሐመድ
አቶ ተሻገር አበራ እና አቶ ጃዋር መሐመድ

የኦሮሞ የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር ባሣለፍነው ቅዳሜና ዕሁድ፤ ጥቅምት 12 እና 13/2009 ዓ.ም. ለንደን ላይ ልዩ ጉባዔ አካሂዶ ነበር።

ስብሰባው የተዘጋጀው በኦሮሚያ ውስጥ እየተፈጠረ ባለው ቀውስ ዙሪያ ለመነጋገር፣ የተለያዩ የኦሮሞ አመለካከቶችን ባገናዘበ መልኩ ውይይት ማድረግና መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር መሆኑን ከጉባዔው አዘጋጆች አንዱ የሆኑት የኦሮምያ ክልል የቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ አበራ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የስብሰባው ተሣታፊዎች የሲቪክ ማኅበረሰቦች አባላት፣ የተለያዩ የፖለቲካ ተቋማት፣ ምሁራን እና በአጠቃላይ በኦሮሞ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ የኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ አዘጋጁ ተናግረዋል።

ተሣታፊዎቹ የኦሮሞ ትግል ምን መምሰል አለበት? እንዴት መራመድ አለበት? ለሚሉ ጥያቄዎች የሐሣብ ልውውጥ ማድረጋቸውንም አቶ ተሻለ አስረድተዋል። በዚህ ሐሳብ ልውውጥ ወቅት የተለያዩ አቋሞች መንጸባረቃቸውና ለቀጣይ ውይይትም መሸጋገራቸውን ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ አቶ ተሻለ አበራንና በጉባዔው ላይ ተገኝቶ የነበረውን በኦሮሞ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ የኢንተርኔት ላይ ተሟጋችና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐመድን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

የለንደኑ ጉባኤ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:27 0:00

XS
SM
MD
LG