በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢንዶኔዥያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ


ጄኔራል ፕራቦዎ ሱቢአንቶ
ጄኔራል ፕራቦዎ ሱቢአንቶ

በኢንዶኔዥያው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸንፌአለሁ ሲሉ በጡረታ ላይ የሚገኙት የጦር ሠራዊት ጄኔራል ፕራቦዎ ሱቢአንቶ አወጁ።

ተቀማጩ ፕሬዚዳንት ጆኮ ዊዶዶ ግን አብላጫውን ድምፅ እንዳገኙ ከወዲሁ የወጡ ቆጠራዎች ይጠቁማሉ።

የጠቅላላ ምርጫው ውጤት በኦፊሴል የሚገለጸው፣ በግንቦት መጨረሻ እንደሚሆን ታውቋል።

በዘንድሮው የኢንዶኔዥያ ብሄራዊ ምርጫ በመላ ሃገሪቱ በተዘጋጁ 809, 563 የድምጽ መስጪያ ጣቢያዎች 193 ሚሊዮን ሕዝብ ድምፁን ሰጥቷል። የምርጫ ኮሚሽኑ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ከ11 ሺህ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የገቡለትን ካርዶች ቆጠራ አጠናቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG