በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢንዶኔዥያ አውቶብስ ተገልብጦ አሥራ ሦስት ሰዎች ሞቱ


ባንቱ በተባለችው አደጋው በደረሰበት ሥፍራ 13 ሰዎችን ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ባንቱ በተባለችው አደጋው በደረሰበት ሥፍራ 13 ሰዎችን ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

በኢንዶኔዥያዋ ጃቫ ደሴት በባህር ዳርቻ ለመዝናናት ይጓዙ የነበሩ የፋብሪካ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አንድ የአስጎብኝ ድርጅት አውቶቡስ ላይ በደረሰ አደጋ እስካሁን የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ሌሎች ቁጥራቸው የበዙ ሰዎች መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

አርባ ሰባቱን መንገደኞች አሳፍሮ ከማዕከላዊ ጃቫ ሱኮሃርጆ ወደ አጎራባች ዮጊያካርታ ግዛት ቤተሰቦች ወደተሰባሰቡበት ሥፍራ በማቅናት ላይ የነበረው አውቶቡስ ሾፌር ተሽከርካሪውን መቆጣጠር አንዳቃተው እና ቁልቁል መንከባለሉን ባልለስልጣናቱ ትናንት ማምሻው ላይ በሰጡት ገለጣ አስታውቀዋል።

«ያነጋገርናቸው የዓይን እማኞች እንደገለጡልን ሾፌሩ ተሽከርካሪውን ለመቆጣተር ጥረት በማደረግ ላይ ሳለ ከቁጥጥር እንደወጣበት እና ክፉኛ መረበሽ ይታይበት እንደነበር ይህም ተሽከርካሪውን ለማቆም የሚረዳው ፍሬን መስራት ማቆሙን አመላካች ነበር" ሲሉ አንድ ባንቱ የተባለችው አደጋው የደረሰበት ሥፍራ የሚገኝባት ወረዳ ፖሊስ ኃላፊ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG