በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህንድ የጠፈር ጣብያ የመመስረት ዕቅድ እንዳላት አስታውቃለች


ህንድ የራስዋን የጠፈር ጣብያ የመመስረት ዕቅድ እንዳላት አስታውቃለች። የህንድ የጠፈር አገልግሎት ሊቀ መንበር ኬ ሴቫን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ህንድ እአአ በ2030 ከ11 ዓመታት በኋላ፣ 20 ቶን የሚሆን የጠፈር ጣብያ የመመስረት ዕቅድ አላት ብለዋል።

ህንድ የጠፈር ጣብያውን ምስረታ በሚመለከት ከማንኛዋም ሀገር ጋር አትተባበርም ሲሉም አክለዋል። የጠፈር ጣብያው የሚያስፈልገው የመጀመርያውን የህንድን የሰዎች የጠፈር በረራን ለመደገፍ ነው ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG