ወደ 60 ሺ የሚጠጋ ህዝብ የተሳተፈበትና 42 ኪ.ሜ የሸፈነው ህዝባዊ ሩጫ በትናንትናው ቀን እሁድ አስመራ ከተማ ውስጥ ተካሂዷል።
ሕዝባዊ ሩጫው 25ኛውን ዓመት ብሔራዊ እዮቤልዩ የኤርትራ ነጻነት ቀን ምክንያት በማድረግ ነው የተካሄደው።
የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና ስፖርተኞችም ተሳትፈዋል።
አትሌቶች ፍረዝግሂ መኮነን፣ መሓመድ ኑር ሑሴንና ተስፋሂወት ገብረትንሳኤ ከአንደኛ እስከ 3ተኛ በመውጣት ከ2,000 እስከ 50,000 ናቅፋ የንዘብ ሽልማት ማግኘታቸውን ባለደረባችን ከአስመራ ዘግቧል።