ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሎራ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሃሪኬን ወይም ከባድ ዝናብ የተቀላቀለበት የአውሎ ነፍስ ማዕበል፣ ዛሬ ማለዳ ላይ በደቡብ ምስራቋ ክፍለ-ሀገር ሊዊዝያና ላይ ካረፈ በኋላ፣ በመጠኑ እንደተዳከመ ተገልጿል። ክፍለ-ግዛቱ ላይ ሲያርፍ፣ አደገኛ የሆነው አራተኛ ደረጃ የተሰጠው፣ የአውሎ ነፋስ ማዕበል ነበር። ከፍተኛው ቁጥር አምስት ነው።
የሀገሪቱ ብሄራዊ የሃሪኬን ማዕከል በገለጸው መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት ሃሪኬን ሎራ፣ በሰዓት 195 ኪሎ ሜትር እየነፈሰ ሲሆን፣ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ወርዷል።