በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄሪኬን ኢያን በፍሎሪዳ ጉዳት አደረሰ


ትናንት ደቡባዊዋ ዩናይትድ ስቴትሷ ፍሎሪዳ ግዛትን ያቋረጠውና “ሄሪኬን ኢያን” የሚል ስያሜ የተሰጠው አደገኛ ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ ያደረሰው ጉዳት
ትናንት ደቡባዊዋ ዩናይትድ ስቴትሷ ፍሎሪዳ ግዛትን ያቋረጠውና “ሄሪኬን ኢያን” የሚል ስያሜ የተሰጠው አደገኛ ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ ያደረሰው ጉዳት

ትናንት ደቡባዊዋ ዩናይትድ ስቴትሷ ፍሎሪዳ ግዛትን ያቋረጠውና “ሄሪኬን ኢያን” የሚል ስያሜ የተሰጠው አደገኛ ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ ያደረሰውን ጉዳት ለመታደግ ዝግጅት እየተካሄደ ሲሆን አደጋው ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ያለ ኤሌክትሪክ ኃይል ያስቀራቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

ባለሙያዎች ሄሪኬን ኢያን ለህይወት አስጊ እንደሚሆንና በማዕከላዊ የፍሎሪዳ ግዛት በከፍተኝነቱ በተመዘገበ ጎርፍ ሊጥለቀለቅ እንደሚችል ትናንት በሰጡትን ትንበያ ማስጠንቀቃቸው ተመልክቷል፡፡

በከባድ ዝናብ የታጀበው አውሎ ነፋስ ዛሬ ሀሙስ አቅሙ እየተዳከመ የመጣ ቢሆንም ነገ ዓርብ ወደ ደቡብ ካሮላይና ግዛት ሲቃረብ እየተጠናከረ የሚመጣ መሆኑን ተነግሯል፡፡

የሰሜን ምስራቅ ፍሎሪዳና እንዲሁም የጆርጂያና የደቡብ ካሮላይና የባህር ዳርቻዎች ከ10 እስከ 20 ሴንቲሜትር የሆነ ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንደሚያገኙ የባለሙያዎች ትንበያ ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG