በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኸሪኬን ዶሪያን


የዩናይትድ ስቴትስ የውቅያኖስ ማዕበል ተከታታይ ብሄራዊ ማዕከል ዛሬ እንዳስታወቀው፣ “ኸሪኬን ዶሪያን” ተብሎ የተጠራው የውቅያኖስ ማዕበል ዛሬ ወደኋላ ላይ እንደሚጠናከር ተናገረ።

ዛሬ ማዕከሉ ባወጣው መግለጫ ዶሪያን በሳምንቱ መጨረሻ ካሪቢያንዋ ባሃማስ አልፎ የፍሎሪዳዋ ሰርጥ ሲደርስ እጅግ አደገኛ ማዕበል ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የባሃማስ መንግሥት ለሰሜን ምዕራባዊው ክፍለ ግዛትዋ ማስጠንቀቂያ ያወጣች ሲሆን የፍሎሪዳ አገረ ገዢ ሮን ደ ሳንቲስም ለመላዋ ፍሎሪዳ አስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል።

ዶሪያን በሰዓት አንድ መቶ ስድሳ አምስት ኪሎ ሜትር ፍጥነት ይዞ እየነጎደ ነው። የፊታችን ሰኞ ማለዳ ቢያንስ በ209 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ደቡብ ምስራቅ ፍሎሪዳን ሊመታ እንደሚችል ተተንብይዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የፌደራል መንግሥት ባለው ዓቅም ሁሉ በዚህ እየተቃረበ ባለው ዝናባማ ማዕበል ላይ ማትኮሩን ለማረጋገጥ ሲሉ በገለፁት ውሳኔያቸው ወደፖላንድ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰርዘዋል፤ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ነው ብለዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG