በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአየር ንብረት ለውጥ ላይ በስዲኒ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ


በመቶዎች የሚቆጠሩ የአየር ንብረት ለውጥን ሂደት ለመገደብ ተጨማሪ ዕርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቁ ሰልፈኞች ዛሬ በሲድኒ አውስትራልያ አዲስ በዓለምቀፍ ደራጃ የሚካሄድ የተቃውሞ ሰልፍ ዙር ጀምረዋል።

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ የተሰባሰቡት የሊበራል ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት በሚገኝበት ኒው ሳውት ዌልስ ሲሆን መንግሥት አዲስ የከሰል፣ የነዳጅ ዘይትና የጋዝ ውጥኖችን እንዲያስወግድ ጠይቀዋል። በበርካታ የእስያ ፓሲፊክ ከተሞችም ብዙ ሌሎች ሰልፈኞች የግሪታ ታንበርግን ጥሪ አስተጋብተዋል። ግሪታ ታንበርግ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ዘመቻ የምታካሄድ የ16 ዓመት ዕድሜ የስዊድን ታወላጅ መሆንዋ ይታወቃል።

የአውስትራልያው የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ያለው የሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ ክፍል ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በመቶዎች በሚቆጠር የሰደድ እሳቶች በተጎዳበት ወቅት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG