በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬንን ለመርዳት ለጋሾች ያሳዩትን ቸርነት ግብረሰናይ ወገኖች ቢያደንቁም የሌሎች ቀውሶች ወጭ ጉዳይ እያሰጋቸው ነው


ፎቶ ፋይል፦ የኦርቶዶክስ እምነት ተከያይ የሆኑ ዩክሬናውያን ምዕመናን በእሁድ የቤተክስቲያን አገልግሎታቸው በቤተክርስትያን ፀሎት ያደርጋሉ፤ ወደ ዩክሬን ለመጓጓዝ የተዘጋጀው ሰብአዊ እርዳታ ጊዜያዊ ማከማቻ በርሊን፣ ጀርመን፤ ሚያዚያ 10/2022
ፎቶ ፋይል፦ የኦርቶዶክስ እምነት ተከያይ የሆኑ ዩክሬናውያን ምዕመናን በእሁድ የቤተክስቲያን አገልግሎታቸው በቤተክርስትያን ፀሎት ያደርጋሉ፤ ወደ ዩክሬን ለመጓጓዝ የተዘጋጀው ሰብአዊ እርዳታ ጊዜያዊ ማከማቻ በርሊን፣ ጀርመን፤ ሚያዚያ 10/2022

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ግዜ አንስቶ ዓለም ለዩክሬን የእርዳታ እጁን የዘረጋበት መጠን ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ዓለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ቢናገሩም የሩሲያ እና የዩክሬን ግጭት፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅና ሌሎች አካባቢዎች በእኩል ደረጃ ትኩረትና ገንዘብ ከሚሹ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታዎች ላይ አቅጣጫ እያስቀየረ ነው ሲሉ ሥጋታቸውን ገልፀዋል።

ሴቭ ዘ ችልድረን በተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም የሚሰሩ አንድ ባለሥልጣን እንደተናገሩት እጅግ በከፍተኛ መጠን የተከሰተው የስደተኛ ቀውስ "ባለተለመደ ሁኔታ" ርህራሄ እና ድጋፍ የተሞላበት ከፍተኛ ምላሽ አግኝቷል ብለዋል። በዋሽንግተን ሆነው የተቋሙን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚቆጣጠሩት ግሪጎሪ ራም እንደሚሉት

"ለሴቭ ዘ ችልድረን፣ ሌሎች ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት የሚመጣው የገንዘብ እርዳታ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የሚያደርገው ድጋፍ፣ መተባበሩ፣ የዩክሬንን የባንዲራ ከለሮች የሚያውለበልቡ፣ በአጠቃላይ የድጋፍ መጠኑ ከዚህ በፊት ያልታየ ነው።"

ሆኖም በዛው መጠን የተዘነጉ ቀውሶች በጣም ብዙ ናቸው ይላሉ ራም።

"በአሁኑ ወቅት ዓለም ግጭቶችን፣ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን፣ እና የኮቪድ ወረርሽኝ እያስተናገደ ነው። ግን የዓለምን ትኩረት ወደ ሱዳን፣ ምስራቅ ኮንጎ፣ ሳህል እና ሌሎች ልክ በዩክሬን ያሉ ህፃናት እየተሰቃዩ ባሉበት መንገድ የሚሰቃዩ ህፃናት ባሉባቸው ቦታዎች ለመሳብ በጣም አስቸጋሪ ነው።"

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመች ግዜ አንስቶ ከ4.6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ዩክሬንን ጥለው ተሰደዋል። በተጨማሪም 7.1 ሚሊየን ሰዎች በሀገር ውስጥ ተፈናቅለዋል። ከነዚህ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ከተፈናቀሉ 11.7 ሚሊየን ሰዎች 7.5 ሚሊየኑ ህፃናት ሲሆኑ - እነዚህ ህፃናት በዓለም ዙሪያ እጅግ የከፋ ግጭቶች በሚካሄድባቸው አካባቢ ከሚኖሩ 190 ሚሊየን ህፃናት መሀከል የሚካተቱ መሆናቸውን ራም ይገልፃሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ግምት እንዳስቀመጠው በዓለም ዙሪያ በዚህ አመት ብቻ 274 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ቁጥር ባለፈው አመት ከነበረው 235 ሚሊየን ሰዎች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ አለው።

በገንዘብ እጥረት ምክንያት የእርዳታ መጠኑን የቀነሰው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ፣ ከፍተኛ የእህል አምራች የሆኑትን ዩክሬን እና ሩሲያን ያማከለው ግጭት በዓለም ዙሪያ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ያልታየ እጅግ የከፋ የምግብ ቀውስ ያስከትላል ሲል አስጠንቅቋል።

ትኩረት የሳበው 'ድንገተኛ ክስተት'

ሜርሲ ኮርፕስ በተሰኘው ሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ ተቋም የናይጄሪያ ተወካይ የሆኑት ሞውሪስ አሞሎ፣ በዩክሬን ለተቀሰቀሰው ቀውስ የተሰጠውን ፈጣን ምላሽ እና አውሮፓ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች አካላት ያሳዩትን ለጋሽነት ያደንቃሉ። ሆኖም ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለምልልስ ሲናገሩ

"አቅርቦቶች እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፎች በዓለም ዙሪያ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው በሚሊየን የሚቆጠሩ የተጎዱ የማህበረሰብ አካላት ወደ ዩክሬን እየተወሰዱ ነው የሚል ሀሳብ ገብቶናል" ብለዋል።

ለምሳሌ፣ ዴንማርክ ከዩክሬን የሚመጡ ስደተኞችን ለማስተናገድ ስትል፣ በዚህ አመት በአፍሪካ ለሚገኙት ቡርኪናፋሶ እና ማሊ ከመደበችው የልማት እርዳታ ላይ 50 ከመቶ እና 40 ከመቶ ለመቁረጥ መወሰኗን ሜርሲ ኮርፕስ ገልጿል። የአሜሪካ ድምፅ መረጃውን ገለልተኛ በሆነ መንገድ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማጣራት አልቻለም።

አማሎ "በድንገተኛ የተከሰተ" ላሉት የዩክሬን ቀውስ እና "ስር የሰደዱ እና በግዜ ሂደት እየተባባሱ የሄዱ" ላሏቸው በአፍጋኒስታን እና ሶማሊያ እንደሚታዩት አይነት ቀውሶች ዓለም እየሰጠ ያለው ምላሽ "እጅግ ከፍተኛ ልዩነት አለው" ይላሉ።

አክለውም ዓለም አቀፍ ሚሊያ የሚሰጠው ትኩረትም እንዲሁ አቅርቦቶች "በግለሰብ ደረጃም ይሁን ለተቋማትና ለመንግስታት" በሚከፋፈሉበት መንገድ ላይ ተፅእኖ አሳድሯል ይላሉ።

ዴቬክስ የተሰኘ በዓለም ዙሪያ በሚከሰቱ ጉዳዮች ላይ መረጃ የሚሰጥ የሚዲያ ተቋም፣ የተለያዩ ሀገራት 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ ድጋፍ ለዩክሬን ለመስጠት ቃል መግባታቸውን መመዝገቡን አስታውቋል።

ሆኖም የገንዘብ መጠኑ በጠቅላላ ለሰብዓዊ እርዳታ ብቻ የሚውል አለመሆኑንና ከህዝብ የተሰበሰበውን እርዳታም እንደማያካትት ጨምሮ ገልጿል።

ይህ በእርዳታ አሰጣጥ ዙሪያ የሚታየው ልዩነት፣ 'አዲስ ሰብዓዊነት' በሚል የተባበሩት መንግሥታት ያቋቋመው ገለልተኛ የዜና ድህረ ገፅ መጋቢት 15፣ 2014 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት ትኩረት ያደረገበት ጉዳይ ነው።

ሪፖርቱ በመጋቢት ወር በተደረገ ገንዘብ የማሰባሰቢያ ጉባኤ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ቀደም ሲል ካደረገችው ድጋፍ በተጨማሪ ስደተኞችን ለሚቀበሉ የአውሮፓ ሀገራት የአንድ ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምትሰጥ ማስታወቋን እና ሌሎች እርዳታ ሰጪ ሀገራትም ከዩክሬን ጋር ተያይዘው ለሚካሄዱ ሰብዓዊ እንቅስቃሴዎች 1.5 ቢሊየን ዶላር ለመስጠት ቃል መግባታቸውን በአፅንኦት አመልክቷል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ የሆኑን ስቴፋን ዱጃሪክ "ይህ ለሰብዓዊ እርዳታ ጥሪ ከተሰጠው ምላሽ ሁሉ እጅግ ፈጣኑ እና ከዚህ በፊት ከተሰጡ እርዳታዎች ከፍተኛ ለጋስነት የታየበት ነው" ማለታቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

ከህዝብ በተሰበሰበ መረጃ መሰረት ዘጠና አራት ከመቶ የሚሆነው ህዝብ በስቃይ ውስጥ እንደሚገኝ በተገለጸበት አፍጋኒስታን ያለው ሁኔታ ግን ከሌላው የተለየ ነው። የተባበሩት መንግስታት ባለፈው ወር እንዳስታወቀው በዚህ አመት በአፍጋኒስታን የሚያስፈልጋውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠት ከተጠየቀው 4.4 ቢሊየን ዶላር እስካሁን የተገኘው 13 ከመቶው ብቻ ነው።

እርዳታ የሚሰጠው እና የማይሰጠው ማነው?

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ለዩክሬን የተለያዩ ሰብዓዊ እና ወታደራዊ እርዳታ የሚሰጡ ሀገራትን ለማሳየት የተጠቀመው የዓለም ካርታ ከአፍሪካ ሀገራት፣ ከላቲን አሜሪካም ሆነ ከደቡብ እስያ ሀገራት የሚመጣ ምንም አይነት ድጋፍ አያመለክትም።

በርግጥ አፍሪካ እርዳታ ሰጪ እንዳትሆን የሚያደርጓት ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች እንዳሉ በደቡብ አፍሪካ የልማት እና አስተዳደር ባለሙያ እንዲሁም መቀመጫውን ዋሽንግተን ባደረገው ዊልሰን የተሰኘ ማዕከል የአፍሪካ ፕሮግራም ውስጥ አጥኚ የሆኑት ቴሬንስ ማክኔም ይገልፃሉ።

"ወረርሽኙ የአፍሪካን ኢኮኖሚ እጅጉን ጎድቶታል። በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የኢኮኖሚ ምንጭ የላቸውም" ይላሉ ማክኔም። ሁለተኛው ምክንያት አፍሪካ ከራሽያ እና ከምዕራቡ አለም ጋር ይዛ የኖረችው ታሪካዊ ግንኙነት ነው። በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የቀድሞው ሶቪየት ህብረት የአፍሪካ ሀገራት ከአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ጋር ከነበራቸው ቁርኝት ነፃ ለመውጣት ያካሂዷቸው ለነበሩ እንቅስቄሶዎች ድጋፍ አድርጓል። በቅርብ ግዜ ደግሞ ሩሲያ ለአህጉሩ የወታደራዊ ሥልጠና፣ መሳሪያ እና የኢኮኖሚ መዋዕለ-ንዋይ መስጠት ቀጥላለች።

ማክኔም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያ በዩክሬን የምታካሂደውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንድታቆም የሚጠይቀውን ውሳኔ በመጥቀስ "ያ ካርታ የማያመለክተው አንድ ነገር ይህ ግጭት በአፍሪካ ውስጥ ምን ያክል ልዩነት እንደፈጠረ ነው" ይላሉ።

የካቲት 23/2014 ዓ.ም ለምርጫ የቀረበው የውሳኔ ሀስባ ከ141 ሀገራት ባገኘው ድጋፍ አልፏል። ከ54 የአፍሪካ ሀገራት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ውሳኔውን ቢደግፉትም፣ 20 የሚሆኑት ድምፀ ተዓቅቦ አድርገዋል ወይም ድምፅ አልሰጡም። ማክኔም "ይህ ለሩሲያ እንደተሰጠ ድምፅ አልባ ድጋፍ ተደርጎ ይቆጠራል" ያላሉ።

አክለውም ተዓቅቦ ካደረጉት ሀገራት "አብዛኞቹ ሙሉ ለሙሉ አምባገነን ወይም ቅልቅል አገዛዝ ያላቸው እና በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ወይም በሶቪየት ዘመን ጠንካራ ግንኙነት የነበራቸው ናቸው" ሲሉ አመልክተዋል።

መቀመጫው በኒው ዩርክ የሆነ የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ውስጥ የአፍሪካ ጥናት አጥኚ የሆኑት አቤኔዘር አባዳሬ የአፍሪካ መንግስታት የሩሲያን ወረራ በግልፅ ለማውገዝ አለመፈለጋቸውን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት በይፋ ፍልሚያውን ባለመቀላቀላቸው እና ለዩክሬን ድጋፍ ባለማሰየታቸው የምዕራብ ሀገራት መጀመሪያ ላይ አሳይተውን የነበረውን ቁጣ አመልክተዋል።

ከዋሽንግተን ወጣ ብሎ የሚኖረውና በትውልድ ናይጄሪያዊ የሆኑት አባዳሬ በመጋቢት ወር ላይ ባሳተሙት ፅሁፍ የምዕራብ ሀገራት የአፍሪካ መሪዎች ዋጋ እንደሌላቸው አርገው እንዳይቆጥሩ፣ ይልቁንም የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ መክረዋል።

ኦባዳሬ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ

"በአፍሪካ ያሉ ሰዎች የሚሉት ሌላ ሀገርን መውረር ትክክል አይደለም ነው። ያንን እንረዳለን ነው።" ካሉ በኋላ ግን ደግሞ "ምዕራቡ ዓለም ራሱ ባስቀመጠው የግብረገብ ትርክት ልክ መገኘት አለበት። ምዕራቡ ዓለም ሁሌም ያንን አያደርግም ... ብዙዎቹ ሀገራት አሳማኝ የሆነ ቅሬታዎች እንዳሏቸው ያስባሉ። እና ደግሞ እነዛን ቅሬታዎች አንስተው ምዕራብ ሀገራት እንዴት መናኛ አርገው ያይዋቸው እንደነበር የመነጋገሪያው ግዜ አሁን ነው ብለው ያስባሉ" ብለዋል።

አፍሪካዊ ርዳታ ሰጪዎች ይረዳሉ

ኦባዳሬ "በአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና በአፍሪካ ህዝብ መሀከል ልዩነት እንዳለ መኖሩን ማወቅ ያስፈልጋል። ተራው ህዝብ ለዩክሬን ህዝብ ድጋፍ አለው።" ይላል።

ከድጋፎቹ መሀከል ጊፍት ኦፍ ዘ ጊቨርስ ወይም የሰጪዎች ስጦታ በተሰኘው የደቡብ አፍሪካ ፋውንዴሽን አማካኝነት የሚደረገው ድጋፍ አንዱ ነው። ፋውዴሽኑ በአህጉሩ ትልቁ መንግስታዊ ያልሆነ ለመቅሰፍቶች ድጋፍ ምላሽ እና እርዳታ ሰጪ ተቋም ሲሆን ዳይሬክተሩ ኢምቲያዝ ሶሊማን አብዛኛውን የገንዘብ ድጋፍ የሚያሰባስቡት ከደቡብ አፍሪካ ነዋሪዎች እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተከትሎ ድጋፍ መስጠት ከጀመሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ድርጅቶች ነው። ሶሊማን

"ለሰዎች ርዳታ የምንሰጠው ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ነው። በዓለም ዙሪያ በየትኛውም አካባቢ ለማንኛውም እርዳታ ለሚፈልግ ሰው እንደርሳለን" ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የትዳር አጋሯ በደቡብ አፍሪካ በሚኖር አንዲት ዩክሬናዊት ሴት ለተጀመረው የዩክሬን ድጋፍ፣ እርዳታ ሰጪዎች ከ100 ሺህ ዶላር ያሰባሰቡ ሲሆን አንድ የርዳታ ሰጪ ተቋም ኪየቭ፣ ካርኪቭ፣ ኪርሰን እና ዛፖሪዪዣን ጨምሮ ቢያንስ ስድስት የዩክሬን ከተሞችን መድረስ እንዲችሉ ማገዙን ሶሊማን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የሰጪዎች ስጦታ ተቋም በሚንቀሳቀስባቸው 43 ሀገራት እንደሚያደርገው፣ በዩክሬንም በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምግቦች፣ ዳይፐር፣ መድሃኒት እና አልባሳትን ይገዛል። በብዙ ሀገራት ውስጥ የጤና እና የትምህርት አገልግሎት ይሰጣል በአደጋ ግዜ ሰዎችን አፈላልጎ የማዳን ምላሽ ይሰጣል።

የሰጪዎች ስጦታ በዩክሬን የሚማሩ አፍሪካውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ገንዘብ ያሰባስባል።

"ይህ አፍሪካ ለአውሮፓ ደራሽነቷን ያሳየችበት በመሆኑ ልዩ ዘመቻ ነው" የሚሉት ሶሊማን፣ አፍሪካ አብዛኛውን ግዜ እንደ ለማኝ፣ ሁልግዜ ኋላ ቀር እና በራሳችን ምንም ማድረግ የማንችል ተደርገን ነው የምንቆጠረው ይላሉ።

ሶሊማን አክለው ሌሎች ህብረተሰቦች "አፍሪካ አሁን ማን ማድረግ እንደምትችል እንዲገነዘቡ እፈልጋለሁ። አፍሪካ አሁን አውሮፖን እየረዳች ነው" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG