በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ዳርፉር ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ጨምሯል ተባለ


ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ ዛሬ ረቡዕ ባወጣው ሪፖርት፣ ሱዳን ዳርፉር ውስጥ በሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ፣ ካለፈው ህዳር ወር ጀምሮ፣ አዲስ የጥቃት ዘመቻ እየደረሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህ መሆኑም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጥቃት የተጎዳውን ይህን አካባቢ ደህንነት እንዲያስከብር አሰችኳይ ፍላጎት መኖሩን ያሳያል ብሏል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርቱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ በታጣቂ ኃይሎች መካከል የሚደረገው ጥቃት በሰላማዊ ዜጎቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ነው ብሏል፡፡

ሪፖርቱ የተባበሩት መንግሥታት የጾታ ጥቃቶችን የሚከታተሉ ባለሙያዎችን ጨምሮ በአካባቢው የሰብአዊ መብት ሁኔታዎችን የሚከታተል አንድ ጠንካራ መርማሪ ቡድን እንዲያሰማራም ጠይቋል፡፡

XS
SM
MD
LG