በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ንግግር በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ዙሪያ


"ሪፖርታችሁን እጠፉ" - የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ................... "አናጥፍም" - ሂዩማን ራይትስ ዋች

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ላይ ያወጣቸውን ሪፖርቶች እንደገና እንዲፈትሻቸው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ አክሎም ሂዩማን ራይትስ ዋች ለዓለም ባንክ ባስገባው ደብዳቤ እንደ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የእምባ ጠባቂ ፅሕፈት ቤትና ብሐራዊ የምርጫ ቦርድ እንዲዘጉ የሚጠይቅ ሃሣብ ማስፈሩ ተቋሙ ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ መርሆች መቆሙን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል ብሏል፡፡

በእነዚህና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሣደር ጥሩነህ ዜናና የሂዩማን ራይትስ ዋች ከፍተኛ ተመራማሪና በአፍሪካ መምሪያ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠሪ ሌስሊ ሌፍኮ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ያነጋገራቸው ሰሎሞን አባተ ነው፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG