ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል በሦስት ምዕራፎች ከፍሎ የጀመረውን ዘመቻ ወደ ማጠናቀቁ መሆኑን በመጥቀስ የህወሓት መሪዎች እጃቸውን እንዲሰጡ የሚያሳስብ መልዕክት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት አውጥተዋል።
የህወሓት መሪዎች ግን መልዕክቱን እያጣጣሉት ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማሳሰቢያ የሚኮንኑና የሚደግፉ በየበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ሁኔታዎችን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ ለማድረግ እንጥራለን እያሉ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡