በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምስተዳርም ውስጥ በእስራኤል የእግር ኳስ ደጋፊዎች ላይ በተካሄደ ጥቃት 5 ሰዎች ሰዎች ተጎዱ

አምስተርዳም ውስጥ በአያክስ እና ማካቢ ቴል አቪቭ መካከል በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ በእስራኤል ደጋፊዎች ላይ ባነጣጠረ ፀረ-ሴማዊ ጥቃት የተጎዱ አምስት ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን የአምስተርዳም ፖሊስ ዛሬ ዓርብ አስታውቋል።

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 62 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ፖሊስ ገልጿል፡፡

የእስራኤል እና የኔዘርላንድ መሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የአይሁድ ማህበረሰብ ቡድኖች ጥቃትና ሁከቱን ሲያወግዙ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ለዚሁ ጉዳይ በፍጥነት ወደ ኔዘርላንድ ተጉዘዋል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአምስተርዳም በእስራኤል ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አውግዘው የኔዘርላንድ ባለስልጣናት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል፡፡

የኔዘርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲክ ስኩፍ “በእስራኤላውያን ላይ የሚደረገው ጸረ ሴማዊ ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ግጭቶች የተነሳ የተባባሰው ዓለም አቀፍ ውጥረት የእስራኤል ቡድኖችን በሚያካትቱ ጨዋታዎች ላይ የደህንነት ስጋቶችን እየፈጠረ መምጣቱ ተነግሯል።

የአምስተርዳም ፖሊስ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ የጥቃት ድርጊቶችን መመርመር መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በከተማው ውስጥ ባሉ የአይሁድ ተቋማትና ከፍተኛ አይሁዳውያን በሚኖሩባቸው ቦታዎች የደህንነት ጥበቃዎች መጠናከራቸው ተመልክቷል፡፡

የአምስተርዳም ከንቲባ ፌምኬ ሃልሴማ ግጭት ሊከሰት ይችላል በሚል ፍልስጤማውያንን የሚደግፉ የተቃውሞ ሰልፎች በስታዲየሙ አካባቢ እንዳይካሄዱ የከለከሉ ቢሆንም በከተማው በርካታ አካባቢዎች ሁከቱ መቀስቀሱን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘግባ አመልክቷል፡፡

በአውሮፓ ሊግ ጨዋታ አያክስ ማካቢ ቴል አቪቭን 5-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG