በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እና ዐርብ፣ በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ ቢያንስ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የወረዳው አስተዳደር ገልጿል።
ገበያተኞችን አሳፍሮ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ግድያው መፈጸሙን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የአቤ ዶንጎሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ከተማ ዋቁማ፣ በተለይ የዐርቡን ጥቃት ተከትሎ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉም አስታውቀዋል፡፡
የወረዳው አስተዳደር፣ ለጥቃቱ በአካባቢው ይንቀሳቀሳሉ ያላቸውን ታጣቂዎች ተጠያቂ ያደረገ ሲኾን፣ በአካባቢው የተከሠተውን የጸጥታ ችግር ለመፍታትም እየሠራኹ ነው፤ ብሏል፡፡
መድረክ / ፎረም