በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ታጣቂ ሠርጎገቦችን ደመሰስኩ አለች


'በሶማሌ ክልል 340 የሚሆኑ የታጠቁ ሽብርተኞችን ከብበን አብዛኞቹን ደምስሰናል'፤ የኢትዮጵያ መንግሥት 'የተለመደ የኢሕአዴግ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡' ኦብነግ

“በግዛቴ በኩል በባሕር ዘልቀው ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ሲሞክሩ ተከብበዋል ሲል የራስአወጅዋ ሶማሌላንድ መንግሥት ሰሞኑን የሰጠውን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት አጠናክሯል፡፡

ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺመልስ ከማል ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ የትግርኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ሺመልስ በዚህ መግለጫቸው በኤርትራ የሠለጠኑ ወደ 340 የሚሆኑ የታጠቁ ኃይሎች በሶማሊላንድ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክሩ ዮኒ ሰደሬ እና ሃሪብ በተባሉ ቦታዎች የሶማሌ ክልል ልዩ የፖሊስ ኃይል እና በአካባቢው ነዋሪዎች የማጥቃት እርምጃ ተወስዶ በቁጥር አብላጫዎቹ ሲደመሰሱ ተራፊዎቹ እጃቸውን መስጠታቸውንና ቆስለውም የተያዙ መኖራቸውን አመልክተዋል፡፡

ወደ አርባ አካባቢ የሚሆኑ ደግሞ የቀሩ መኖራቸውን አሁን ተከብበው እንደሚገኙም አቶ ሺመልስ ተናገረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ የኢትዮጵያው ባለሥልጣን የሰጡትን መግለጫ “ከእውነት የራቀ ነው” ሲሉ አስተባብለውታል፡፡ “ከኤርትራ የመጣም ሠራዊት የለንም” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሠራዊታቸው በአካባቢው አሁንም እየተዋጋ መሆኑንና ሰሞኑን ከሃምሣ በየሚበልጡ የኢትዮጵያ ወታደሮችና አንድ ስማቸውን ያልጠቀሷቸውን ኮሎኔል መግደሉን አቶ ሃሰን አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ሐሙስ መስከረም 3 ቀን ጀምሮ በተካሄደ ውጊያም በሁለት አጋጣሚዎች ከራሣቸው ወገን 11 ተዋጊዎች መገደላቸውንና አንድ የሠራዊታቸው አባል ቆስሎ መማረኩን ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን የቪኦኤ ሪፖርት ያድምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG